Contact Us

Use the form on the right to contact us.

You can edit the text in this area, and change where the contact form on the right submits to, by entering edit mode using the modes on the bottom right. 

(416) 781-4802

About Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
--------------------------------------------------------------

Ethiopia, the land of Judeo-Christianity, is one of the most ancient predominantly Christian countries of the world. It is marked with a fascinating history, unique civilization, culture and religious life. The Book of Genesis recounts: “And the name of the second river is Ghion: the same is it that compasses the whole land of Ethiopia” (Geneses 2:13). The Psalmist David also says: “Let Ethiopia hasten to stretch out her hands to God” (Psalms 68:31).

አጽዋማት እና በዓላት


በዓለ ክብሩ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
Dec
26
3:00 PM15:00

በዓለ ክብሩ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS

በዓለ ክብሩ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል

ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም  አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ  ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ (ዳን.10፡5-9)

ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በብሉይ ኪዳን በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው(ዳን.5፡11)ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ መልአክ ነበር፡፡ ለዚህ ነቢይ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡(ዳን.9፡21-22) አሁንም ነቢዩ ዳዊት “አቤቱ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ብፁዕ ነው፡፡ በልቅሶ ሸለቆ በወሰንኸቸው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፡፡”(መዝ.83፡5-6)እንዳለው በቅድስና ሕይወት በመጽናታቸው ምክንያት ቅዱስ ገብርኤል መምህር የሆናቸው ቅዱሳን ብዙዎች ናቸው፡፡ የእኛ እውቀት በሰማያት ከትመው ካሉት ቅዱሳን መላእክት እውቀት ጋር ሲነጻጸር እኛን እንደ ሕፃናት ያደርገናል፡፡ እኛ የእነርሱን እውቀት ገንዘባችን የምናደርገው በትንሣኤ ነው፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ “ዛሬ በመስታወት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፡፡ አሁን በከፊል ኋላ ግን እንደተገለጠልኝ መጠን ሁሉን አውቃለሁ”(1ቆሮ.13፡12)ብሎ አስተማረን፡፡ ስለዚህም እውቀታችን የተሟላ እንዲሆንና ሰይጣንን ለመቃወም እንድንበቃ የቅዱሳን መላእክት የእውቀት ድጋፍ በእጅጉ ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም ከእኛ ይልቅ ሳጥናኤልን የሚያውቁት እነርሱ ናቸውና፡፡ እንዲህም ስለሆነ ጌታችን በእውቀታቸው እኛን እንዲረዱን ለእያንዳንዳችን  ጠባቂ መልአክትን ሰጠን፡፡(ማቴ.18፡10፤ሉቃ.13፡6-9)

ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱን ሁሉ ሲያስገዛለት በትዕቢት ተሞልቶ “በኃይሌ  አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም  የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም አወስዳቸዋለሁ፤ከእኔም የሚያመልጥ የለም የሚቃወመኝም የለም፡፡”(ኢሳ.10፡13-14) ብሎ በመታበይ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ ዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ አቆመው፡፡ በግዛቱ በልዩ ልዩ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉትን ሹማምንቱንና ገዢዎችን ሰበሰባቸው፤ “የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናና የዋሽንትን የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ወድቃችሁ ንጉሥ ናብከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል ስገዱ፡፡ ወድቆም ለማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣል” ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህን አዋጅ የሰሙ የንጉሥ ሹማምንት ሁሉ የመለከቱና የእንቢልታው እንዲህም የዘፈን ድምፅ በተሰማ ጊዜ ተደፍተው ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡

በባቢሎን አውራጃዎች ላይ የተሾሙ አዛርያ(ሲድራቅ)፣ አናንያና(ሚሳቅ) ሚሳኤል(አብደናጎ) ግን ንጉሥ ላቆመው ምስል አልሰገዱም፡፡ ነገር ሠሪዎችም ይህንን ወሬ ለንጉሥ ነገሩት፤ ንጉሥም እጅግ ተቆጥቶ ወደ እርሱ አስጠራቸው፡፡ እርሱ ላቆመው ለወርቅ ምስል ያልሰገዱ እንደሆነ እጅና እግራቸውን ታስረው ወደ እቶን እሳቱ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን  “ናብከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አንፈልግም፡፡ ንጉሥ ሆይ! እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፣ ከሚነደውም ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፤ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን አንዳናመልክ፣ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” ብለው መለሱለት፡፡ የንጉሥ ናብከደነፆር ቁጣ ከፊት ይልቅ እጅግ ነደደ እሳቱንም ሰባት እጥፍ እንዲያቀጣጥሉና እነዚህን ሦስት ብላቴኖች እጅና እግራቸውን አስረው ከእነ ማዕረግ ልብሳቸው ከእቶን እሳት ውስጥ እንዲጨምሩአቸው ትእዛዝን አስተላለፈ፡፡ ትእዛዙ አስቸኳይ ነበርና እነርሱን ወደ እሳቱ የጣሏቸውም ኃያላን በእሳቱ ወላፈን ተገርፈው ሞቱ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሳለ ግን ሠልስቱ ደቂቅ ወደ አምላካቸው “በፍጹም ልባችን እናምንሃለን፣ እንፈራሃለን፣ አታሳፍረን እንጂ ገጸ ረድኤትህንም እንፈልጋለን፡፡” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ጸሎታቸውን ተቀበለ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንም ከመጣባቸው መከራ ይታደጋቸው ዘንድ ላከው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም እስራታቸውን ፈታ፤ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዘቀዘው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅም መልአኩን ልኮ ከዚህ እቶን እሳት ያዳናቸውን አምላክ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ስምህም ለዘለዓለም የተመሰገነና የከበረ ነው” በማለት አመሰገኑት፡፡

ንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር የሰው መልክ ያለው ነገር ግን አምላክን የሚመስል መልአክ ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ “ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን”(ዮሐ.11፡49) ብሎ እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም “እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ ምንም የነካቸው የለም፤የአራተኛውም መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል” ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው ያለው በኋላም መልአክ ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ እርሱ ስለመሆኑ ለነቢዩ ዳንኤል በተገለጠበት ግርማ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡

ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን “እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የአገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡ ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ፡፡(ዳን.3 በሙሉ)

ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መንጎቹዋ የእምነትን ፍሬ ከእነዚህ ብላቴኖች ተምረው እግዚአብሔርን በማምለክ እንዲጸኑና የመልአኩን የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት እንዲረዱ በታኅሣሥ 19 ቀን ይህን ዕለት ትዘክራለች፤ በታላቅ ድምቀትም ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እምነት በድርጊት ሊታይ የሚገባው ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ የሚል ሁሉ ካመነበት ጊዜ አንስቶ ክርስቶስን መስሎ ለመኖር ሊተጋና መስሎ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡ በሠልስቱ ደቂቅ  የታየው እምነት በአንድ ጀምበር የተገነባ እምነት ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ በአንድ እግዚአብሔር ታምነው በቅድስና ሕይወት በመመላለስ የመጣ እምነት ነው፡፡ እነዚህ ብላቴኖች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኙትን የድል አክሊል ተስፋ አድርገዋልና አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል የነደደውን የእሳት እቶን አላስፈራቸውም፤ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው ጽኑ እምነት በእሳት ተቃጥለው ለመሞት እንኳ አስጨከናቸው፡፡ እንዲህም ሆነው በመገኘታቸው በእምነታቸው እግዚአብሔርን ደስ አሰኙት፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ባለሟሉን ቅዱስ ገብርኤልን በመላክ ከእሳቱ እቶን ታደጋቸው፡፡

የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

View Event →
Dec
12
12:00 AM00:00

በአታ ለማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS

በአታ ለማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ

ሰይጣን በእባብ አካል ተሰውሮ ሔዋንን፤ በእርሱዋም አዳምን በማሳት በእነርሱ ላይ ሞት እንዲሠለጥንባቸው ስላደረገ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፣ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደረጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኮናውን ትነድፋለህ” በማለት የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ፈረደበት፡፡ “በአንተ” የተባለው ሰይጣን ሲሆን፣ “በሴቲቱ” የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት (ገላ.4፡4)፣ “በዘርህ” ሲል የዲያብሎስ የግብር ልጆችን ሲሆን(ዮሐ.8፡49)፣ “በዘርዋ” የተባለው ክርስቶስ ነው(ገላ.3፡16)፡፡ ትርጉሙ እንዲህ አንደሆነም ወንጌላዊው ዮሐንስ “ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የጠበቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ”አለን፡፡(ራእ.12፡17) እባብ የተባለው ሰይጣን ስለመሆኑም “ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ”(ራእ.12፡9) ብሎ ጻፈልን፡፡

አዳም በዚህ ፍርድ ቃል ምክንያት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ምን እንደሆነ ተረዳ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክ በሔዋንና በእርሱ ላይ የፈረደው ፍርድ እነርሱን ከማዳን አንጻር የርኅራኄ ፍርድ እንደሆነ፤ እርሱና ሔዋን በክፉ ምርጫቸው ምክንያት ያጎሳቆሉትን ተፈጥሮአቸውን ወደ ቀደሞው ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ንጽሕት ዘር ከሆነች ታናሽ ብላቴና እንደሚወለድና በመስቀሉ ሞት በእነርሱ ላይ የተላለፈውን የሞት ፍርድ እንደሚሽረው፣ አዳምና ሔዋን የተመኙትን የአምላክነት ስፍራ በክርስቶስ በኩል እንደሚያገኙት እንዲሁም በእርሱ የማዳን ሥራ የመለኮቱ ተካፋዮች እንዲሆኑ አስተዋለ፡፡  ይህም እውን እንደሚሆንም “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” በሚለው አምላካዊ ቃሉ አረጋገጠ፡፡ ስለዚህም ለመሰናከሉ ምክንያት የሆነችው ሴት ለትንሣኤውም ምክንያት እንደሆነች ተረዳ፡፡ በዚህም ምክንያት አስቀድሞ ከሥጋዬ ሥጋ ከአጥንቴ አጥንት የተገኘሽ ክፋዬ ነሽ ሲል “ሴት” ብሎ የሰየማትን ሚስቱን “ሔዋን” ብሎ ስም አወጣላት፡፡ ትርጓሜውም የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው፡፡ እንዲያ ባይሆንና አባታችን አዳም ይህንን የእግዚአብሔርን አሳብ ባይረዳ ኖሮ እንዴት በሰው ዘር ላይ ሞት እንዲሠለጥን ምክንያት ለሆነችው ሚስቱ ሔዋን የሚል ስምን ያወጣላት ነበር? ነገር ግን በእርሱዋ ሰብእና ውስጥ እርሱንና ወገኖቹን ከሞት ፍርድ ነጻ የሚያወጣቸውንና ወደ ቀደመው ክብራቸው የሚመልሳቸውን ጌታ በሥጋ የምትወልድ፣ የሕያዋን ሁሉ እናት የሆነች ንጽሕት ዘር እንዳለች ከእግዚአብሔር የፍርድ ቃል አስተዋለ፡፡

አዳም ይህን ሲረዳ ክፋዩ ለሆነች ሚስቱ ያለው ፍቅርና አክብሮት ከፊት ይልቅ ጨመረ፡፡ ከእርሱም በኋላ ለሚነሡ ወገኖቹም ለመዳናቸውና ለመክበራቸው ምክንያት ከሴት ወገን የሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም እንደሆነ አስተውለው ወንዶች ለእናቶቻቸውና ለእኅቶቻቸው እንዲሁም ለሴት ልጆቻቸው ተገቢውን አክብሮትና ፍቅር እንዲያሳዩ ለማሳሰብ ሲልም ሚስቱን ሔዋን ብሎ መሰየሙንም መረዳት እንችላለን፡፡ እንዲህም ስለሆነ ነቢዩ ኢያሳይያስ “ዐይኖችን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሟቸዋል”(ኢሳ.60፡4)ብሎ ትንቢት ተናገረ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ራሱዋን የጌታ ቤተክርስቲያን በማድረግ፤ ቤተክርስቲያን በልጁዋ ክቡር ደም ተዋጅታ እንድትመሠረት ምክንያት ሆናለች፡፡ ስለዚህም አባታችን አዳም እንዳደረገው ነቢዩም እንደተናገረው ለእርሱዋ ያለንን ፍቅርና አክብሮት በጾታ ለሚመስሎአት እናቶቻችን፤ እኅቶቻችን፣ እንዲሁም ሴቶች ልጆቻችን በማሳየት እንገልጠዋለን፡፡

ከአዳም በኋላ የተነሡ ቅዱሳን አበው በአዳምና በሔዋን መተላለፍ ምክንያት በእነርሱ ላይ የሠለጠነባቸው ሞት የሚወገድላቸውና ወደ ገነት የሚገቡት እግዚአብሔር አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለድ እንደሆነ ከአዳም አባታቸው ተምረው ነበር፡፡ ስለዚህም ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ተካፋይ ለመሆን እሾኽና አሜካላ በምታበቅለውና ሰይጣን በሠለጠነባት በዚህ ምድር የመዳን ተስፋቸው የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማርያምን መወለድ በተስፋ እየተጠባበቁ ቅዱስ ጳውሎስ “ማቅ፣ ምንጠፍና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ተጨነቁ፣ ተቸገሩ፣ መከራ ተቀበሉ፣ ተራቡ፣ ተጠሙም፣ ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናቸው፤ዱር ለዱርና ፍርኩታ ለፍርኩታም ዞሩ”(ዕብ.11፡33-38) በጽድቅ ተጉ፡፡ ጌታችንም እንደተስፋ ቃሉ ከንጽሕት ቅድስት እናቱ ተወልዶ በመስቀል ላይ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በመቅረብ ወደ ገነት አፈለሳቸው፡፡ ስለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዳ ጌታችንን መድኀኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እስክትወልድ ድረስ የተስፋ ቃሉ እንዳልተፈጸመ ለማስዳት ሲል ጨምሮ “እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙም፡፡ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ አግዚአብሔር ስለ እኛ የምትበልጠውን አስቀድሞ በይኖአልና፡፡” ማለቱ(ዕብ.11፡39-40)

አባቶቻችን ከሐዋርያት በትውፊት አግኝተው እንደጻፉልን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልክ እንደ ይስሐቅ፣ ነቢዩ ሳሙኤል እና መጥምቁ ዮሐንስ፣ መካን ከነበሩ ወላጆች የተገኘች ናት፡፡ እናቱዋ ሐና በአባቱዋ በኩል ከአሮን ቤት ስትሆን በእናቷ በኩል ከይሁዳ ወገን ነበረች፡፡ አባቱዋ ኢያቄም ግን ከይሁዳ ወገን ነበር፡፡ እነዚህ ወላጆች በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ነገር ግን ልክ እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ እስከ እርጅናቸው ድረስ ልጅ አልወለዱም ነበር፡፡ በአይሁድ ዘንድ መካንነት የእርግማን ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ስለነበር ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔር አምላክ ልጅ በመስጠት ይህን ስድብ ያርቅላቸው ዘንድ በቅድስናና በንጽሕና በመጽናት ምጽዋትንም በማብዛት በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጸሎታቸውንና ምጽዋታቸውን እግዚአብሔር ስለተቀበለላቸው አምላክን በሥጋ በመውለድ ለዓለም መድኅን የሆነቸውን ቅድስት ድንግል ማርያምን በእርጅና ዘመናቸው ግንቦት አንድ ቀን ወለዷት፡፡ ማርያም ማለት የእግዚብሔር ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሐናም እግዚአብሔር አምላክ ስድቤን ከእኔ አርቆልኛልና ከእግዚአብሔር እንዳገኘዋት ለእግዚአብሔር መልሼ እሰጣታለሁ ብላ የተሳለቸውን ስለት አሰበች፡፡ ሦስት ዓመት ሲሞላትም ስለቷን ትፈጽም ዘንድ ከኢያቄም ጋር ልጇን ቅድስት ድንግል ማርያም ይዛ ወደ ቤተመቅደስ አመራች፡፡ በጊዜው ሊቀ ካህናት የነበረው ካህኑ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ በታላቅ ደስታ ተቀበላቸው፡፡ ነገር ግን ካህኑን ዘካርያስን የምግብናዋ ነገር አሳስቦት ነበረና ሲጨነቅ ሳለ ነቢዩ ኤልያስን ይመግበው ዘንድ መልአኩን የላከ እግዚአብሔር አምላክ(1ነገሥ.19፡6) እናቱ የምትሆነውን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይመግባት ዘንድ ሊቀ መላእክትን ቅዱስ ፋኑኤልን አዘዘላት፡፡ ካህኑ ዘካርያስም የምግቡዋ ነገር እንደተያዘለት ሲረዳ በቤተ መቅደስ ውስጥ እንድታድግ አደረጋት፡፡ ይህ እለት በሁሉም ኦሬንታልና የሐዋርያት የሥልጣን ተዋረድ(Apostolic succession) በተቀበሉ የሚታወቅና የሚከበር ክብረ በዓል ሲሆን  በአታ ለማርያም ወይም የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም “ልጄ ሆይ ስሚ፣ ጆሮሽንም አዘንቢዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፤ እርሱ ጌታሽ ነውና፡፡”(መዝ.44፡10) የሚለው ቃል መፈጸሙን እናስተውላለን፡፡

የጌታን መወለድ በተስፋ ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን አበው ይህች ቀን እጅግ ታላቅ እለት ነበረች፤ ምክንያቱም የመዳናቸው ቀን  መቃረቧን የምታበሥር ቀን ነበረችና፡፡ ለእኛም ለክርስቲያኖች ይህች ቀን ታላቅ የሆነ በረከት ያላት ናት፡፡ ሙሴ የመገናኛ ድንኳኗንና በውስጡ ያሉትን ነዋያተ ቅዱሳት የጥጃና የፍየሎች ደምን ከውኃ ጋር በመቀላቅል በቀይ የበግ ጠጉርና በሂሶጵ በመንከር ረጭቶ ቀድሶአት ነበር፡፡(ዘጸ.24፡7-8፤ዕብ.9፡18-22) ንጉሥ ሰሎሞንም እርሱ ያሠራውን ቤተመቅደስ እርሱና ሕዝቡ ባቀረቡት የእንስሳት መሥዋዕት ቀደሷት ነበር፡፡(1ነገሥ.8፡23) እነዚህ ሥርዐታት ግን ክርስቶስ በደሙ ለሚዋጃት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነበሩ፡፡

በዚህች ቀን ቅድስት እናታችን ራሱዋን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ የብሉዩዋ ቤተመቅደስ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን ልትተካ መቃረቡዋን ለማብሠር ወደ ቤተ መቅደስ ያመራችበት ቀን ነው፡፡ ጌታችንም ከእርሱዋ የነሳውን ሥጋና ነፍስ በተዋሕዶ የራሱ ቤተመቅደስ በማድረግና እኛንም በጥምቀት የአካሉ ሕዋሳት እንድንሆን በማብቃት ሥጋችንን የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የቅድስት ድንግል ማርያምን ወደ ቤተመቅደስ መግባት ባሰብን ቁጥር እግዚአብሔር ቃል ከእርሱዋ በሥጋ በመወለዱ ያገኘነውን ድኅነትና ብዙ ጸጋዎችን እናስባለን፡፡ አሁን እኛ ክርስቲያኖች በጥምቀት ከእርሱዋ የተወለደውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለብሰነዋል፤ (ገላ.3፡27) ከእርሱዋ በነሣው ተፈጥሮ በኩል ሞትን በመስቀሉ ገድሎ ሲያስወግደው፣ እኛም በጥምቀት ከእርሱ ሞት ጋር በመተባበራችን ሞትን ድል የምንነሣበትን ኃይልን ታጥቀናል፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ጸጋ ሠርተንበትና አብዝተነው ብንገኝ ከትንሣኤው ተካፋዮች መሆንን እናገኛለን፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጸመልን እግዚአብሔር ቃል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለዱ ምክንያት ነው፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም ብሉይን ከአዲስ ያገኛኘች መንፈሳዊት ድልድይ ናት፡፡ በብሉይ ያሉት ቅዱሳን በሐዲስ ኪዳን ካለነው ጋር አንድ ማኅበር የፈጠሩትና ከቅዱሳን መላእክትም ጋር እርቅ የወረደው ከእርሱዋ በነሳው ሰውነት በኩል ነው፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም”(ኤፌ.2፡19) ብሎ አስተማረ፡፡ ራሷን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ እኛንም በልጁዋ በኩል የመንፈሱ ቤተ መቅደስ እንድንሆን ምክንያት ሆናልናለችና የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት ለእኛ ክርስቲያኖች ልዩ ትርጉም አለው፤ ስለዚህም ይህቺን እለት በታላቅ ድምቀት እናከብራታለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም

ረድኤትና በረከት ያሳትፈን

ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ 

View Event →
Dec
5
11:30 AM11:30

የኢትዮጵያዊው ጻድቅ የአቡነ ሀብተማርያም በዓል

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS
Annual Feast of Abune Habte-Maryam.JPG

አቡነ ሀብተማርያም

፩ – የትውልድ ታሪካቸው

የቅዱስ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም ትውልድ ሀገር የራውእይ የምትባል ምስራቃዊት ሀገር ውስጥ ሲሆን የኢትዮጵያ ንጉስ እስክንድር በነገሰ በሺ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት ዓመተ ምህረት ፍሬ ብሩክ የሚባል አንድ ሰው በዚች ሀገር ውስጥ ነበር፡፡ ይኸውም ከከበሩም ሰዎች ተለይቶ ብዙ ገንዘብ ያለው ባለጸጋ ነበር፡፡ በህጋዊ ጋብቻ ስሟ ዮስቴና የምትባል ሴት አገባ ይህችውም ሴት በደግ ሥራ ሁሉ የተሸለመች ያጌጠች ነበረች፡፡ እነዲህ ባለ ሥራ ሳለች መንፈሳዊ ሀሳብ እንዲህ ሲል ተነሳባት ለአንቺ በዚህ ዓለም መኖር ምን ይረባሻል ዛሬ የሚያልፍ የሚጠፋ ነውና የሚመሰገንበት ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ሌላ ዓለም ይገለጣልና % ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢነዳ በነፍሱ ከተጎዳ ምን ይጠቅመዋል እንዳለ” ማቴ. 16÷26፣ ማር. 10÷36፡፡ ለአንቺ ግን በሰማይ ፀንቶ መኖርን ሁለተኛዋን ሀገር መያዝ ይሻላል የሚል ሀሳብ መጣባት፡፡ ይህን ካሰበች በኋላ ፈጥና ተነስታ በሌሊት ከቤት በመውጣት በሀገሯ አንፃር ትይዩ ወደ ሆነው ከጅቦች፣ ከነብሮች፣ ከዓሳማዎች፣ ከጦጦችና ከዝንጀሮዎች በስተቀር ምንም ምን ወደ ማይኖርበት በረሀ ደረሰች፡፡ በዚያም ደጃፏ ያልተዘጋ ትንሽ ዋሻ አገኘች፡፡ በዋሻው ውስጥም መዝሙረ ዳዊትን በአንክሮ የሚደግም ክቡር ባህታዊ አየች ባየችውም ጊዜ ደነገጠች እርሱም ሴቲቱን ባያት ጊዜ ፍርሀት መንቀጥቀጥ በላዩ ላይ ወረደበት፡፡ መጀመሪያ ስትገባ የጋኔን ምትሀት መስላው ነበርና ሰው መሆኗን ባወቀና በተረዳ ጊዜ ተቆጣት፡፡ እሷም ቤቴን ንብረቴን ያለኝን ሁሉ ትቼ መጥቻለሁ በዓለም ውስጥ ያለውን ሁሉ ንቄ እመንን ዘንድ እወዳለሁና ስለዚህም ወደዚህ ምድረበዳ መጣሁ አለችው፡፡ ይህም ባህታዊ በትህትናና በፈሪሀ እግዚአብሔር ይህን የሚያስደንቅ መልካም መልስ በመለሰችለት ጊዜ አንድ ሰዓት ያህል ካሰበ በኋላ ምንኩስናስ የለሽም ነገር ግን በፍቅር በአንድነት ወደ ቤትሽ ወደ ህጋዊ ባልሽ በሰላም ተመለሽ የተፈቀደልሽን እነግርሻለሁ ከህጋዊ ባለቤትሽ ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ይሆናል የገድሉና የትሩፋቱ ዜና እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል በህይወተ ስጋ ሳለ በፈጣሪው እግዚአብሔር ፍቃድ የብዙዎችን ሰዎች ነፍሳት ከሲኦል ያወጣል እንደ መላእክትም ክንፈ ፀጋ ተሰጥቶታል፤ በሰው አካል ከስጋ ሆኖ ሳለ በተመስጦ ወደ ሰማይ የሥላሴን የአንድነትን የሦስትነትን ምስጢር ያያል አላት፡፡ ቅድስት ዮስቴናም ከአረጋዊ ባህታዊው ይህን ነገር ሰምታ አደነቀች የፈጣሪዬ ፈቃድ ከሆነ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ አለች፡፡ ጥቂት ወራት ከቆየችም በኋላ መልኩ እንደ በረዶ ነጭ እንደ ፅጌረዳም ብሩህ ቀይ የሆነ መልከ መልካም ገፁ ብሩህ የሆነ ልጅ ወለደች ይህ ህፃን በግንቦት ወርህ በ26 ቀን በተወለደ ግዜ በአባቱና በእናቱ ቤት ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡ ይህ ቅዱስ ህፃንም 40 ቀን በሞላው ጊዜ በኦሪትና በሉቃስ ወንጌል እንደተፃፈ በእግዚአብሔር ፊት ያቆሙት ዘንድ ወደ ካህን አቀረቡት፡፡ ክህኑም ለክርስትና አባቱ አሳልፎ ሰጠው ስሙንም ሀብተማርያም ብሎ ሰየመው ከዚህም በኋላ እናት አባቱም ተመለሱ፡፡ ይህ ቅዱስ ህፃን እግዚአብሔርን በመፍራት አደገ ከዕለታት አንድ ቀን ካህናቱ በቤተክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱእግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ እያሉ ሲፀልዩ ሰምቶ በልቡ ይህች ፀሎት በጣም ጥሩ መልካም ፀሎት ናት እኔ ይህችን ፀሎት መርጫታለሁ በዚህ ዓለም ከአሳች ህሊና በሚመጣውም ዓለም ከገሀነም እሳት እንድንድንባት አውቃለሁ አለ ስግደትንም እንደፈጣን ፈረስ ሩጫ ብዙ እስኪያልበው ድረስ ይሰግድ ነበር፡፡

 ፪  – አባታችን አቡነ ሀብተማርያም በሕይወት ሳሉ ካረፉም በኃላ ያደረጉት ተአምራት

አባታችን አቡነ ሀብተማርያም በሕይወት ሳሉም ሆነ ካረፉ በኋላ እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራትን አድርገዋል፡፡ ከነዚህ መካከልም በጥቂቱ እንመልከት፡፡ የአቡነ ሀብተማርም አባት ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያምን ከዕለታት በአንድ ቀን የበግ ጠባቂ አደረጓቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን በኋላ ለብዙዎች ቅዱሳንና በዓለም ለሚኖሩ ምዕመናን በጎቹ ጠባቂ ያደርገው ዘንድ ወዶ መርጦታልና ያቀን እስኪደርስ ፈጣሪያችን ሀብትማርያምን ይጠብቀው ነበር በዚህም ዕለት በጎች ሲጠብቅ ብዙ የሚሆኑ የበጎች እረኞች እሸት ተሸክመው መጥተው ና እሸትን እንብላ አሏቸው፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተምርያም ግን እኔስ አልበላም አሏቸው፡፡ እነርሱ እኛ ብላ ስንልህ ስለምን አትበላም አሉት አባትችንም ይህንን እሸት ከየት እንዳመጣችሁት ምንም እንደሆነ ስለማላውቅ ነው አላቸው (መጽሐፍ ኅጥእ ሰው እግዚአብሔርን የሚፈራውን ይንቀዋል ያቀልለዋል ብሎ እንደተናገረው) እረኞቹም አባታችንን በቁጣ ዓይን አዩዋቸው ብዙም ተቀጣጡባቸው ከዚህም በኋላ ከፊታቸው ተቀምጠው ያን ሰርቀው ያመጡትን እሸት መብላት ጀመሩ እሸቱንም በልተው ከጨረሱ በኋላ አባታችን ቅዱስ ሀብተማርያም በእነዚያን በግ ጠባቂዎችን የማንችለው ፅኑ ዝናብ መጥቷልና ወደየቤታችን እንግባ ከዚህም የምንጠጋበት ቤት ወይም ዋሻ የለምና አላቸው እረኞቹም ለኛ የማይታይ ለአንተ እንዴት ይታያል ብለው ተሳለቁባቸው፡፡

ቅዱስ ሀብተማርያምም የጥበብ አምላክ ልቡን በፀጋ መንፈስ ቅዱስ አበርትቶታልና እኔ የማውቀውን እናንተ አታውቁም ነገር ግን ወደየቤታችሁ ተመልሳችሁ በጊዜ ግቡ አሏቸው እነርሱም አንተ እራስህ ተመልሰህ ወደ ቤትህ ግባ እኛ ግን ፀሀይ ገና ቀትር እያለ ተመልሰን ወደ ቤታችን አንገባም አሉት፡፡ ይህንንም ባሉት ጊዜ በፍጥነት እየሮጠ በጎቹንም እያስሮጠ ወደ ቤቱ ገባ፡፡ ወደ ቤቱም ከገባ በኋላ ፅኑ ዝናብ መጣ ንፋስም ነፈሰ እነዛም አረኞች ይህ ሁሉ በላያቸው ላይ እየተፈፀመ ሳለም አልሸሹም ነበር፡፡ እግዚአብሄርም ክፋታቸውን አስቦባቸዋልና በላያቸው ላይ የጥፋት ውሀ አወረደባቸው ሁላቸውም ይህንን የጥፋት ውሀ እስኪፈፀምባቸው ድረስ አልተነቃነቁም ነበርና ሁሉም አለቁ፡፡

በዚህም ሌሊት ቃል ከሰማይ ሶስት ጊዜ ሀብተማርያም  ሀብተማርያም ሲል ጠራው ይህም ህፃን አባቱ በአጠገቡ ተኝቶ ነበርና አባቱ የጠራው መስሎት አባቴ ሆይ አለሁ ሲል መለሰ፡፡ ይህንንም ማለቱ ቀድሞ በኤሊ ሊቀ ካህናት ጊዜ እንደተፈፀመ ሆኖበት ነው ሳሙ. 3÷3፡፡ እንደዚህም ሁሉ እግዚአብሔር ይህንን ህፃን ሀብተማርያም እያለ ሶስት ጊዜ ጠራው፡፡ ህፃኑም ሀብተማርያም ተነስቶ ታጥቆ እጅ ነስቶ እንደ ሳሙኤል ጌታዬ ባርያህ ይሰማል በል ተናገር አለው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከአሁን ጀምሮ ግን በግ ጠባቂዎች ከእርሻቸው ያልሆነውን ከሌላ እርሻ የሆነውን እሸት አምጥተው ብላ ቢሉህ አልበላም በላቸው፡፡ እናንተ ግን ብትወዱ ሄዳችሁ ብሉ በኋላ ግን ገሀነም ትገባላችሁ በእሳት ትቃጠላላችሁ በላቸው እንተን ግን ለሚሰሙ ለመረጥካቸው ቃሉን ትነግራቸው ዘንድ ከእኔ ጋር በሚስጢር ትነጋገር ዘንድ መርጬሃለሁ አለ፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ለቃልህ እታዘዝ ዘንድ እሺ ብያለሁ አለው የጠራውም ቃል ስሜንም በኋላ እነግርሃለሁ ነገር ግን የምልህን ቃልና ትዕዛዝ ጠብቅ አለው ዮሐ. 15÷10፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ዳግመኛ በጎቹን እየጠበቀ ሳለ ብዙም የበጎች እረኞች አብረውት ሳሉ አንድ የበግ ጠባቂ መጥቶ የአቡነ ሀብተማርያምን በትር በጉልበቱ ነጥቆት ሄደ፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ተከትሎ ያን በግ ጠባቂ በትሬን ለምን ትቀማኛለህ ቢለው ያም በግ ጠባቂ በጉልበቴ ነጥቄሃለሁ አለው፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም በጎቼን የምጠንቅበት በትሬን እንዳትወስድብኝ በህያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ ዳግመኛም አላምልህም እቋቋምህም ዘንድ ሀይል የለኝምና አለው፡፡ ያም በግ ጠባቂ በትእቢት እንቢ አልኩህ አለው አቡነ ሀብተማርያምም ከእንግዲህ ወዲህ አምልህ ዘንድ አልደግምም ነገር ግን በአንተ ላይ የሚደረገውን ሀይልና ተዓምር አንተው ታያለህና ብሎ ዝም አለ፡፡ ያም በግ ጠባቂ በህዋው በተሰቀለ ጊዜ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሀብተማርያም ሆይ ማረኝ እያለ ይጮህ ጀመር፡፡ ስመ እግዚአብሔርንና የፃድቁ ሀብተማርያምን ክብር ንቆ አቃሏልና ላዩ ታች ታቹ ላይ ቀኙ ግራው ግራው ቀኙ ሆኖ በአየር ተሰቅሎ ዋለ፡፡

በዚ የነበሩ የበግ ጠባቂዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው በጣም አደነቁ፡፡ እነርሱም አባታችን አቡነ ሀብተማርያምን ያደረጉትን ተአምር አይተዋልና እረኛውን እንዲምረው አሁንም አምላክን ስለወለደች ንዕድ ክብርት ስለምትሆን ስለ እመቤታችን ብለህ ማርልን አሉት ቅዱስ አባታችንም የሰቀልኩት እኔ ነኝን ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አማልኩት እንጂ የሃይሉንም ፅናት ያሳየው ዘንድ የሰቀለው እግዚአብሔር ነውና እርሱ ሁሉን ቻይና ይቅርባይ አምላክ ከተሰቀለበት ያውርደው አላቸው፡፡ አባታችንም ይህን ቃል በተናገረ ጊዜ የበግ ጠባቂው ከተሰቀለበት ወርዶ በእግሩ ቆመ በግ ጠባቂዎችም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ለዘመዶቻቸውና ለወገኖቻቸው ያዩትን ተአምር ከመጀመሪያው  እስከመጨረሻው ተናገሩ፡፡ ይህንንም ተአምር የሀገሩ ሰዎች ሰምተው አደነቁ ይህ ታላቅ ፃድቅ ልጅ ነው በፊትም ቢሆን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ እያለ ሲፀልይና  እንደፈጣን ፈረስ ኮቴ ፍጥነት ሲሰግድ ፊቱንም በድንጋይ እየመታ የክርስቶስን ህማማት አስቦ ሲጋደል አይተነዋል ብለው መሰከሩ፡፡ 

– ለአባታችን አቡነ ሀብተማርያም የተሰጣቸው ቃልኪዳኖች

አባታችን አቡነ ሀብተማርያም አራቱ ወንጌላት ከማንበብ ጋር ድካምና ተጋድሎ በበዛ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በቀኝና በግራ አስከትሎ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሲስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ በገሀድ ታየው ጌታችንም ወዳጅ ሀብተማርም ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን ባለው ጊዜ ከፈጣሪ ግርማ የተነሳ ደንግጦ ከመሬት ወደቀና እንደ በድን ሆነ ጌታችንም ክቡራት በሚሆኑ እጆቹ አንስቶ በፊቱ መንፈሰ ህይወትን አሳደረበት፡፡ ጌታችንም አቡነ ሀብተማርያምን ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ድካምህና ገድልህ ሁሉ ለዘለዓለም መታሰቢያ ሊሆን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተፅፎልሃል ብዬ በእውንት እነግርሀለሁ ለአንተ ለወደድኩህና ለመረጥኩህ ለወዳጄ የማትዮስንና የማርቆስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ሁሉ ተጭነህ  ወደ ምትሄድበት ቦታ ሁሉ የሚያደርስህ የብርሀን ሰረገላ እሰጥሀለሁ እንዳንተ ላሉ በዋሻ ከሚኖሩ ከመረጥኳቸው ቅዱሳን ትገናኝ ዘንድ ወደ ምስራቅ ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜን ወደ ደቡብ ትሄድበት ዘንድ የብርሀን ሰረገላ ሰጥቼሀለሁ ከሰው ፊት ከተሰወሩ ባህታዊያን ጋር ኑር ዳግመኛ የሉቃስንና የዩሀንስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ በእነርሱ ተጭነህ ስጋዬን ደሜን ለመቅመስ ኢየሩሳሌም ትደርስ ዘንድ የእሳት ሰረገላ ሰጥቼሀለሁ፡፡ በፀሎትህ አምኖ በጎ ስራ ለሚሰራልህ ሁሉ በህይወት ሳለህ ልብስህን በመስጠት ወይም ምግብ ወይም እግር በማጠብ ወይም እንጨት ሣር በማቅረብ ወይም ውሀ በመቅዳት በመርዳት ለደከሙ ሁሉ እምርልሀለሁ ብዬ ቃልኪዳን ሰጥቼሀለሁ፡፡ በህይወቱ ሳለ ለሚሻ መልካሙን ስራ ሁሉ አደርግለታለሁ ከሞትም በኃላ መንግስተ ሰማያትን አወርሰዋለሁ በባለሟልነት እቀበላለሁ ከአንተ ጋርም ደስ እሰኘዋለሁ፡፡ አንተ ከሞትክም በኃላ ስምህን የጠራውንና ዝክርህን የዘከረውን ሁሉ የሀብተማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በህሊና ያሰበውን በልቦና የወሰነውን እፈፅምለታለሁ ሰውን ከቸነፈር ከተቅማጥ እኮእሳት መቃጠል መብረቅ በረሀብ ከሞት እንዲያድን እንደ ሀዋርያት ስልጣን ቃልኪዳን ተሰጠው፡፡ አንትን ገድልህን ቃልኪዳንህን የናቀውንና ያቃለለውን ሁሉ ፍፁም መበቀልን እበቀለዋለሁ፡፡ ወደ መከራ ቦታ አወርደዋለሁ በበጎ ሳይሆን በመዓት አይን እመለከተዋለሁ፡፡ ጠላቶችህን ይበቀልልህ ወዳጆችህን ይጠብቅልህ ዘንድ መልዕክተኛዬ ቅዱስ ሚካኤልም ዘወትር አይለይህ የሰጠሁህን ቃልኪዳን እንዳልነሳህ በራሴ ማልኩልህ፡፡ እንደ ወዳጄ እንደ ፈቅጦርም በእናቴ በድንግል ማርያም አተምኩህ፡፡ ፈቅጦርን ከሰማዕታት ሁሉ አብልጬ እንደወደድኩት አንተንም ከመነኮሳት ሁሉ አብልጬ ወድጄሀለሁና ይህ የሰጠሁህ ቃልኪዳኔ ለዘላለም ይሁንልህ አለው፡፡

በፃድቁ አባታችን በአቡነ ሀብተማርያም በቃል ኪዳናቸው ፀንተን እንድንገኝ የልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

View Event →
Nov
24
to Jan 7

የነቢያት ጾም መጀመሪያ ቀን ነው

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS
First Day of the Fast of the Prophets.JPG

ጾመ ነቢያት 

ዘመኑ ጾመ ነቢያት የተባለበት ምክንያት ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለ ተፈጸመበት እንዲሁም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምሥጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ እየተመለከቱ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡ ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ ወደ ግብፅ ስለ መሰደድ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለመጠመቅ፣ በትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ትንሣኤው፣ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፤ ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ446 ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡

ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር «የማያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር» ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩት እነ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡ ኢሳ 58-1፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለ ተፈጸመበት ይህ ጾም «የነቢያት ጾም» ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡

ዘመነ ስብከት

ከታኅሣሥ 7 ቀን እስከ ታኅሣሥ 13 ቀን ድረስ ያሉት ዕለታት ናቸው፡፡ ምን ጊዜም ወደ ታኅሣሥ 6 አይወርድም ወደ 14ም አይወጣም፡፡ ስብከት ማለት ዐዋጅ ትምህርት ማለት ነው፡፡ ይህም ከልደተ አብርሃም እስከ ልደተ ዳዊት ያለው ትውልድ የሚታሰብበት ፤ ሙሴ በኦሪት፣ ነቢያት በትንቢት፣ ዳዊት በመዝሙሩ በብዙ ምሳሌ ይወርዳል ይወለዳል ሲሉ የተናገሩት የሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ መዝ.143-7 ፤ ኢሳ 64-1፡፡ የሚዘመረው መዝሙር «ወልደ መድኅነ ንሰብክ ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ፤ ከዓለም በፊት የነበረውንና መድኃኒት የሆነውን ወልድን እንሰብካለን» የሚል ነው ቅዱስ ያሬድ፡፡ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት የተናገሩለትንና ሱባዔ የቆጠሩለትን ሐዋርያት ያላቸውን ትተው ተከተሉት ፈቃዱንም ፈጸሙ፡፡ ስለዚህ ምእመናን ክፉ ሐሳባቸውን አርቀው ርኩሰትን አስወግደው ፍጹም ለእግዚአብሔር እንዲገዙ ትምህርት ይሰጣል፣ ስብከት ይሰበካል፡፡ የሚነበበውም ምንባብ ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡ ዮሐ.1-44-49 ፤ ዕብ.1-1-2፡፡

ብርሃን

ከስብከት ቀጥሎ ያለችው ሰንበት ስትሆን እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አስተምህሮ ከልደተ ዳዊት እስከ ፍልሰተ ባቢሎን ያለው 14 ትውልድ ይታሰብበታል፡፡ ክቡር ዳዊት «አቤቱ ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ» /መዝ. 42-3/ እያለ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ከርሱ ወገን እንዲወለድ ትንቢት ስለተናገረ ይህ የሚታሰብበት ነው፡፡ ነቢዩ ዓለም በጨለማ ስለሆነች ብርሃንህን ላክ፣ ሐሰትና የሐሰት አባት ነግሦባታልና እውነትህን ላክ አለ፡፡ ወልድን ላክልን ማለቱ ነው፡፡ ይህንም ቅዱስ ዮሐንስ «ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ» ብሎ ሲመሰክር ጌታም ራሱ «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም» ብሎ ተናግሯቸዋል፡፡ ዮሐ. 8-12 እንዲሁም ብርሃንን እውነት ማለቱ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ ላክልን ሲል ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ስደድልን ማለቱ ነው፡፡
ከጨለማ ወደ ብርሃን አውጣን፣ ሥጋህንና ደምህን ስጠን ሲልም ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚዘመሩት መዝሙራት «ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት ወይዜንዎ ለጽዮን በቃለ ትፍሥሕት፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፣ የምስጋናን ቃል ለጽዮን የሚነግራት ወልድ በክብር፣ በጌትነት እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ነገረ፤ አስታወቀ፡፡» የሚሉ ናቸው፡፡ ንስሐ ከመግባት ቸል እንዳይሉ ይነግራቸዋል፡፡ ነቢያት የጥል ግድግዳን ሰብሮ መለያየትን አጥፍቶ ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚያወጣቸውን ሽተው ውረድ ተወለድ አድነንም እያሉ ጮኹ፣ እውነተኛ ብርሃን ጌታችን ጊዜው ሲደርስ ወደ ዓለም ወጣ፡፡ በመምጣቱም በጨለማ ያለው በብርሃን እንዲገለጥ ለሰው ልጆች እግዚአብሔርን የሚያውቁባት ዕውቀት ተሰጠች፡፡

ኖላዊ

ኖላዊ ተብሎ የሚጠራው ከብርሃን ቀጥሎ ያለው ሳምንት ነው፡፡ የቃሉ ፍች እረኛ ማለት ነው፡፡ እረኞች ለበጎቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ሣር ውኃ ሳያጓድሉ እንዲጠብቁ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በነፍስ በሥጋ የሚጠብቅ ቸር እረኛ ነው፡፡ ይኽንን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሲያብራሩ ከፍልሰተ ባቢሎን እስከ ልደተ ክርስቶስ ድረስ ያለው 14 ትውልድ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ ዘመን እሥራኤላውያን ከሀገራቸው ተሰደው በባቢሎን 70 ዘመን ከኖሩ በኋላ ዘሩባቤልን አንግሦላቸው ይዟቸው እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ከዚያ በፊት እሥራኤል ጠባቂ እንደሌለው መንጋ ተበታትነው ሲኖሩ ነቢያት ከኪሩቤል ላይ የሚገለጥ እረኛቸው እንዲገለጥ የእሥራኤል ጠባቂያቸው ሆይ፣ አድምጥ እያሉ የጠየቁበት መታሰቢያ ነው፡፡ መዝ.79-1-3፡፡

መዝሙሩም «ኖላዊ ዘመጽአ ውስተ ዓለም ወልዱ ወቃለ እግዚአብሔር ዘወረደ እምላዕሉ፤ የእግዚአብሔር ልጅና ቃሉ የሆነ ክርስቶስ ከላይ የወረደ ወደ ዓለም የመጣ እረኛ» የሚል ሲሆን የሚነበበው ደግሞ አንቀጸ አባግዕ የተባለው የዮሐንስ ወንጌል ክፍል ነው፡፡ ዮሐ.10-1-22፡፡ እረኛ የሌለው በግ ተኩላ ነጣቂ እንዲበረታበት በበደሉ ከትጉኅ እረኛው የተለየው የሰው ልጅም በሲኦል አጋንንት በርትተውበት ሲጠቀጠቅ ኖሯል፡፡ እንዲሁም ከመንጋውና ከእረኛው የተለየ በግ እንዲቅበዘበዝ አምላኩን ዐውቆ አምልኮቱን ከመግለጽ የወጣው ሕዝብ በየተራራው መስገጃዎችን እየሠራ የሚታደገውን አምላክ በመፈለግ ሲንከራተት ኖሯል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ «እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር» እንዳለ፡፡ 1ኛ ጴጥ.2-25፡፡ ነቢያት በዓለም ተበትነው የሚቅበዘበዙትን ሕዝቡን በቤቱ ሰብስቦ የሚጠብቃቸው እውነተኛ ቸር እረኛ እንዲወለድ ስለተናገሩ ያን ለማስታወስ ሳምንቱ ኖላዊ ተባለ፡፡

ገሃድ/ ጾመ ድራረ ጥምቀት

ይህ ጾም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ መጾም ነው፡፡ ይህም ማለት በጥምቀት ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው፡፡ የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነም የጥምቀትን ድራር መጾም ነው፡፡ ሐዋርያት «ልደት ጥምቀት ዓርብ ረቡዕ ቢውል በሌሊት ቀድሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበሉ፤ ከሌሊቱ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጹሙ ብለው አይፍረዱ» ብለዋል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/፡፡ የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የጥሉላት ምግብ በጠዋት በመብላት ምእመናን በዓሉን እንዲያከብሩ ታዟል፡፡

ይህም እነዚህ ሁለቱ ታላላቅ የእግዚአብሔር በዓላት በመሆናቸው ነው፡፡ የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማክሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል፡፡ በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ሥራ ይከናወናል፡፡ የጥምቀትን ዋዜማ ጥሉላት መባልዕትን መተው ነው፡፡ ይህንንም እንደ ዘይቤው ገሀድ ይለዋል፣ መገለጫ፣ ግልጥ፣ ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ጋድ ይለዋል፣ ለውጥ፣ ልዋጭ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ረቡዕ ዓርብ ሲውል በዚያ ለውጥ ማክሰኞ ሐሙስ ይጾማልና ጋድ አለው፡፡ እንዲሁም አንድ ጊዜ ሲጾም አንድ ጊዜ ሲቀር እንዳይረሳና ቅዳሜ ወይም እሑድ በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም፣ ነገር ግን እህል ውኃ እንጂ ጥሉላት ከመብላት መጠበቅ ይገባል፡፡

ልደት የሚውልባቸው ረቡዕና ዓርብ ቢሆኑ የፍሥክ /የሚበላባቸው/ ቀናት ሆነው እንዲከበሩ ሐዋርያት ያዘዙ ቢሆንም በዋዜማው የሚገኙት ማክሰኞና ሐሙስ ከጾመ ነቢያት ጋር የተያያዙ ስለሆኑ መጾማቸው ግድ ነው፡፡ ሆኖም የነቢያትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች በመላው የጾሙ ቀናት ሲበሉ ቆይተው በዋዜማው ብቻ ገሀድ ነው ብለው ይጾማሉ፡፡ ነገር ግን ለጾመ ነቢያት ገሀድ የለውም፡፡ ጾሙ የጥምቀት ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለጾመ ነቢያት ገሀድ እንዳለው የሚናገሩም አሉ፡፡ ለዚህም የሚያቀርቡት ማስረጃ እስከ ምሽት መጾሙን ነው፡፡ ይህም «አድልው ለጾም፤ ለጾም አድሉ፡፡» እንዲሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ቢጾም የሚያከራክር ወይንም ስህተት ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን መረዳት ይገባል፡፡

ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ቃል ይፈጸም ዘንድ የሰው ልጆችም ድኅነት ማረጋገጫ እውን ይሆን ዘንድ እንደ ጾሙ እንደ ጸለዩ በልደቱም እንስሳት፣ ሰዎች እንዲሁም መላእክት በአንድነት በደስታ እንደዘመሩ የእኛም ደስታ የተረጋገጠበት ነው፡፡ በመሆኑም በፍቅር፣ በጾም በጸሎት ዛሬም እናስበዋለን፡፡ ነቢያት በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን፡፡ ለዚህም አምላካችን ይርዳን አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

View Event →
Aug
19
6:00 AM06:00

በዓለ ደብረ ታቦር (ነሐሴ ፲፫)

ታቦር ወኤርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ" መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት

"እግዚኦ እግዚእ ሠናይ ለነ ሀልዎ ዝየ፡-ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው" ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ

"ደብረ ታቦር" የሁለት ቃላት ጥምር ገጸ ንባብ ስለሆነ የቋንቋ ሊቃውንቱ ለእያንዳንዱ ቃል የሚሰጡትን ትንታኔ በማስቀደም እንመልከት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደብርን ሲተረጉሙ፡-

ደብር፡- ተራራ፣ ጋራ ገምገም፣ የምድር ዕንብርት ጉብር፣ ታላቅ ረዥም ከወግር የሚበልጥ፣ ደብረ ዘይት፣ ደብረ ሲና፣ ደብረ ታቦር፡፡ አድባረ እስራኤል /ሕዝ. 6፡2/

 • የተራራ ተራራ፣ ከተራራ ሁሉ የሚበልጥ በረዶ የሚፈላበት ሰው የማይደርስበት እንደ ዳሽን፣ እንደ ሄርሞን ያለ የሰማይ ጎረቤት፡፡ አድባረ አራራት፤ አድባረ ነዋኋት ዘመትሕተ ሰማይ /ኩፋ. 8፤ ዘፍ. 7፡19 ፤ 8፡4/
 • ወሰን ድንበር መዲና ከተማ ታላቅ ሀገረ፡- ወኮነ አድባሪሆሙ ለከነዓን እምነ ሲዶን እስከ ጌራራ፣ ደብረ አህጉር ዲበ ኩሉ አድባሪከ፡፡ አድባረ ግብጽ /ዘፍ.10፡19፤ ኢያ. 14፡15 ፤ ዘፀ. 10፡4 ፤ ኢሳ. 1፡26/
 • ገዳም ቤተክርስቲያን፣ ታላቁም ታናሹም ደብረ ሊባኖስ፤ ደብረ ዐስቦ፤ አድባራት ወገዳማት አባ መቃርስ ዘደብረ አስቄጥስ ወዳልወ አልባብ ተሰምየት እስከ ዮም ደብሩ.../ገድለ ተክለሃይማኖት፤ ስንክሳር ዘመጋቢት 27/
 • ደብር ማለት በተራራ ላይ የሚሠራ ተራራ የሚያህል ታላቅ ማለት ነው፡፡ ... በማለት መጽሐፋዊ ማረጋገጫዎችን አስደግፈው ሐተታ ጨምር ትርጉም ሰጥተውታል፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ /አለቃ/፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡ 1948ዓ.ም፡ አዲስ አበባ፡ ገጽ. ከ336-337 ይመልከቱ)

"ታቦር" በናዝሬት አጠገብ የሚገኝ የተራራ ስም ነው፡፡ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ ደቡብ በኩል 10 ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ የተራራ ስም ነው፡፡ ተራራው 572ሜ ከባሕር ወለል ከፍ ይላል፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 113)

የሥነ ቋንቋ ሊቃውንቱ አሁንም የታቦርን ትርጉምና መልከዐ ምድራዊ አቀማመጥ በተመለከተ በመጻሕፍቶቻቸው አብዝተው አትተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጥቂቱን እንመልከት፤

"ታቦር"፡- በፊልስጥኤም በሰማርያ አውራጃ በገሊላ ወረዳ የሚገኝ ሀገር ጌታ ለሐዋርያቱ ምስጢር መለኮቱን የገለጠበት የደብረ ታቦር ስም /ታቦር ወአርምንዔሞ በስመ ዘአከ ይትፌስሑ/ታቦርና ኤርምንዔም በአንተ ስም ደስ ይላቸዋል፡፡ /ከሳቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ከተሰማ ሀብተ ሚካኤል ግጽው ተደርሶ የተጻፈ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት 1951ዓ.ም ገጽ 624/"

"ታቦር"፡- የተራራ ስም ታላቅ ረዥም ተራራ በናዝሬት አጠገብ በስተምስራቅ ያለ ጌታ ምስጢረ መንግስቱን ለነቢያት ለሐዋረያት የገለጸበት / መሳ.4፡6፤ 12፤ መዝ.88/፡፡ በዓለ ዕርገት ወበዓለ ኅምሳ ወበዓለ ታቦር ዘቦቱ ተወለጠ ወአእመሩ አርዳኢሁ ስብሐተ መለኮቱ ወሪደሙ እምደብር እምደብረ ታቦር አዛዞሙ አይንግሩ ዘርእዩ በደብረ እስከ እመ ይትፌጸም በዕድሜሁ /ፍ.ነ.19፤ ድጓ.ሠለ/፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ /አለቃ/መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ አርቲስቲክም ማተሚያ ቤት 1948ዓ.ም አዲስ አበባ ገጽ 892)

ከዚህ የሊቃውንቱ ሰዋስዋዊ ትንታኔ ደብር ማለት ተራራ ቤተ ክርስቲያን ተብሎ እንደሚተረጎም፤ ታቦር ማለት ደግሞ የአንድ ትልቅ ተራራ መጠሪያ ስም መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በመሆኑም፡-

 • ደብረ:-ማለት ተራራ፣ ቤተ ክርስቲያን ማለት ሲሆን
 • ታቦር፡-ማለት የረዥም የተራራ ስም... ከሆነ ሁለቱም ሲናበቡ ደግሞ ማለትም "ደብረ ታቦር"ሲሆን ታቦር የተባለ ተራራ ማለት ይሆናል ማለት ነው፡፡

በዚህ ታቦር በሚባል ረዥም ተራራ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱ የታየበት፣ ምስጢረ ሥላሴ የተገለጸበት፣ ሙሴና ኤልያስ ከብሔረ ሙታንና ከብሔረ ሕያዋን ተጠርተው ስለ ወልደ እግዚአብሔር መድኃኒትነት፣ ጌትነት፣ አምላክነት...የመሰከሩበት የተቀደሰ ተራራ በመሆኑ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይህንን መንፈሳዊ በዓል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ሌሊቱ በሰዓታት፣ በማኅሌት፣ በቅዳሴ፣ በትምህርት... ስታከብር በተገለጸበት ተራራ ስም በደብረ ታቦር ሰይማ ስለሆነ በዓሉ "በዓለ ደብረ ታቦር"በማለት ይጠራል፡፡ በደብረ ታቦር የተገለጸው ምስጢር፣ የታየው ተአምራት...የሚዘከርበት፣ የሚወደስበት፣ የሚተነትንበት...ዕለት በመሆኑ የበዓሉ ስም በዓሉ በተፈጸመበት ተራራ እንዲጠራ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊትና ጥንታዊት እንደመሆንዋ መጠን ለሐዋርያዊ ተልዕኮዋ መሳካት የሚያገለግሏት /የሚረዷት/ከፍተኛ ክብር ያላቸውና በከፍተኛ መንፈሳዊ ትሩፋት የምታከብራቸው "ዓበይት በዓላተ እግዚእ"የጌታ ትላልቅ በዓላት እና ንኡሳን በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ የጌታ ታላላቅ በዓላት አንዱ በየዓመቱ ነሐሴ 13ቀን የምናከብረው የደብረ ታቦር በዓል ነው፡፡ ሙሉ ታሪኩን ከዚህ ቀጥለን እንመልከት፤ የደብረ ታቦር ታሪክ በማቴ. ምዕ.17፡1፤ ማር.9፡1፤ ሉቃ.9፡28 ይገኛል፡፡

የማቴ.ምዕ. 17፡1-9 ንባብ

"ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ፡፡ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም ሙሴና ኤልያስ ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱ ለአንተ አንዱ ለሙሴ አንዱ ለኤልያስ እንሥራ አለው፡፡ እርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው እነሆም ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱም ስሙት የሚል ድምጽ መጣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር፡፡ ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡ ከተራራው በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው"

የአንድምታ ትርጉም

በቂሳርያ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ "መነ ይብልዎ ሰብእ ለወልደ እጓለ እመሕያው"ሰዎች የሰው ልጅን ማን እንደሆነ ይሉታል / ማቴ. 16፡13/ ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ በሰባተኛው ቀን ስምንቱ ደቀመዛሙርቱን ከእግረ ደብር /ከተራራው ሥር/ ትቶ ሦስቱ ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር (ታቦር ተብሎ ወደ ሚጠራው ረዥም ተራራ) ወጣ፡፡ ስምንቱ ደቀ መዛርቱን ከእግረ ደብር ትቶ ሦስቱን ብቻ ይዞ የመውጣቱ ምስጢር ከስምንቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር ይሁዳ ስለ ነበረና "ያአትትዎ ለኅጥእ ከመ ኢይርአይ ስብሐተ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ክብር፤ ልዕልና፣ ምስጢረ መለኮት፣ ምስጢረ ሥላሴ... እንዳያይ ኃጢአተኛውን ያስወግዱታል" የሚል ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡

ይህን ታላቅ አስተርእዮ ምስጢረ መለኮት /የመለኮት ምስጢር መገለጥ/በሌሎች ቦታዎችና ተራራዎች ሳያደርግ መርጦ በዚሁ በደብረ ታቦር እንዲፈጸም የፈቀደበት ምክንያትም በነቢየ እግዚአብሔር በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት እንዲፈጸም ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ "ታቦር ወኤርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ ፤ ወይሴብሑ ለስምከ፤ መዝራዕትከ ምስለ ኃይል፡- ታቦርና ኤርምንኤም በአንተ ስም ደስ ይላቸዋል፤ ስምህንም ያመሰግናሉ፤ ክንድህ ኃይል ከማድረግ ጋራ ተገልጦላቸው"/መዝ.89፡12/በማለት ትንቢት ምስለ ውዳሴ ተናግሮ ስለነበረ ይህንን ምስጢር በደብረ ታቦር ተፈጽሞአል፡፡

አንድም በዚህ ተራራ /በደብረ ታቦር/ ባርቅ ሲሳራን ድል የነሳበት /መሳ. 4፡6-14/ ቦታ በመሆኑ፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣን ድል የሚነሳበት ተራራ ስለሆነ ምስጢርን ከምስጢር ጋር ለማገናኘት ምስጢረ መለኮቱን በደብረ ታቦር ገለጸ፡፡ መልኩም በፊታቸው ተለውጦ ከፀሐይ ሰባት እጅ አበራ፤ ልብሱም እንደ በረድ ፀዓዳ /ነጭ/ሆነ ማለትም ቅድመ ዓለም የነበረ፤ ዓለምንም አሳልፎ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ የሚኖር ብርሃነ መለኮቱ ገለጸላቸው፡፡

ወናሁ አስተርአዩ ሙሴ ወኤልያስ እንዘ ይትናገሩ ምስሌሁ፡- ሙሴ ከብሔረ ሙታን ከመቃብር ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጥተው ከጌታችን ጋር እየተነጋገሩ ተሰሙ፡፡ ሙሴ "የእኔ የሙሴን ጌታ ማን ሙሴ ነው ይለሃል፣ እግዚእ ሙሴ /የሙሴ ጌታ/ ይበሉህ እንጂ፤ እኔ ባሕር ብከፍል፤ ጠላት ብገድል፣ ደመና ብጋርድ፣ መና ባወርድ...እስራኤል ከክፋታቸው መልሶ ማዳን አልተቻለኝም፤ ለአንተ ግን መልሶ ማዳን ይቻልሃል" እያለ ከጌታው ጋር ሲነጋገር ተሰምቷል፡፡

አንድም ሙሴ ወደ ደብረ ታቦር የመምጣቱ ምስጢር አስቀድሞ እስራኤላውያን ከባርነት ለማውጣት ሲጠራ "አርእየኒ ገጸከ" ፍትህን /ክብርህን/ አሳየኝ ብሎ አምላኩን ሲጠይቅ ፊቴን አይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው ሰው የለምና ፊቴን ማየት አትችልም፡፡ "ጀርባዬን ግን ታያለህ" በኋላ ዘመን በመዘነ ሥጋዌ ግን ሥጋ ተዋሕጄ ሰው ሆኜ ስወለድ ታየኛለህ /ዘጸ. 33፡18-23/ ባለው ቃሉ መሠረት ሙሴ የሥግው ቃል አምላኩ ፊት ለማየት ወደ ደብረ ታቦር ጠርቶታል፡፡

ኤልያስም፡- "የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ይልሃል፤ እግዚኦ ኤልያስ /የኤልያስ ጌታ/ ይበሉህ እንጂ፤ አንድም እኔ ሰማይ ብለጉም፣ እሳት ባዘንም...እስራኤልን ከክፋታቸው መልሶ ማዳን አልተቻለኝ፤ ላንተ ለመድኃኒተ ዓለም ግን እስራኤልን መልሶ ማዳን ይቻለሃል"እያለ ሲናገር ተሰምቷል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ምስጢረ መለኮት፣ ማለትም የጌታ በብርሃነ መለኮት ማሸብረቅና ልብሶችም እንደበረዶ ነጭ መሆን እንደዚሁም የእነዚህ የቅዱሳን የነቢያት መምጣት እና ንግግር ከሰማ በኋላ "እግዚኦ እግዚእ ሠናይ ለነ ኃልዎ ዝየ፡-ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡ ቅዱሳን ነቢያቱ የወትሮ ሥራቸውን እየሠሩ ማለትም ሙሴ ደመና እየጋረደ፣ መና እያወረደ፣ ባሕር እየከፈለ፣ ጠላት እያስገደለ... ኤልያስም ሰማይ እየለጎመ፣ እሳት እያዘነመ፣ ዝናመ እያቆመ... አንተም አምላካዊ የመዳን ሥራን እየሠራህ ገቢረ ተአምራትህን እያሳየህ... በዚህ በተቀደሰ ቦታ "በደብረ ታቦር" መኖር ለእኛ እጅግ መልካም ነው"፡፡ "ወእመሰ ትፈቅድ ንግበር በዝ ሠለስተ ማኅደረ አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ ለኤልያስ" አምላካዊ ፈቃድህስ ከሆነ በዚህ ተራራ ላይ አንድ ለአንተ፤ አንድ ለሙሴ፤ አንድ ለኤልያስ ሦስት ዳስ እንሥራ ብሎ ጠየቀ፡፡ "ወእንዘ ይትናገሩ መጽአ ደመና ብሩህ ወጸለሎሙ" ይህንን ሲናገሩ ብሩህ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው ከደመናውም "ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ፡-ልመለክበት የወደድኩት ለምስጢረ ተዋሕዶ የመረጥኩት የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት" የሚል ቃል መጣ፡፡ በዚህም የሥላሴ ምስጢር ለዓለም ለሦስተኛ ጊዜ ተገለጸ፡፡

እግዚአብሔር አብ ደመናን ተመስሎ "የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው"እያለ፣ እግዚአብሔር ወልድ ሥጋን ተዋሕዶ ፍጹም አምላክ ሲሆን ፍጹም ሰውም ሆኖ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነጭ ተመስሎ ተገልጸዋል፡፡

የሥላሴን ምስጢር የተገለጸው ሦስት ጊዜ ነው፡፡

አንደኛ፡- በብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ጊዜ ሥላሴ በወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ተገልጾዋል፡፡ አብ ለአጽንኦ፣ ወልድ ለተዋሕዶ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሆ፣ በድንግል ማርያም ተገልጸዋል፡፡

ሁተለኛ፡- በዮርዳኖስ ተገልጸዋል፡፡ አብ በደመና "ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር" እያለ፣ ወልድ በባሕር ዮርዳኖስ እየተጠመቀ፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ ተገልጸዋል፡፡

ሦስተኛ፡- በደብረ ታቦር በዚህ ዓይነት ምስጢር ተገልጸዋል፡፡

ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሥላሴ መገለጽን አስመልክቶ፤
በላዕሊኪ ወበዮርዳኖስ ወበታቦር ሥልሰ ጊዜያተ
ዘአልቦ ተውሳኮ ወአልቦ ሕፀተ
ለውሉደ ሰብእ ያርኢ ዘሥላሴሁ ገጻተ

ጽጌኪ ድንግል ተአምሪሁ ከሠተ
ወበፀዳሉ አብርሀ ጽልመተ... በማለት በምስጢር አትቶ በምስጋናዊ ቅኔ ደርድሮ በመተርጎም አስቀምጦት እናገኛለን፡፡

ደቀመዛሙርቱም ይኸንን የመለኮትነቱን ድንቅ ምስጢር በዓይናቸው አይተው፣ በጀሮአቸውም ሰምተው እጅግ ተደነቁ፣ ደነገጡ፣ አብዝተውም ፈሩ፡፡ መደኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይህንን የልባቸው ፍርሐትንና ድንጋጤ ተመልክቶ ቀርቦ ዳሰሳቸውና ተረጋጉ፡፡ በመጨረሻም "አዘዞሙ እግዚእ ኢየሱስ እንዘ ይብል ኢትንግሩ ወኢለመኑሂ ዘርኢክሙ እስከ አመ ይትሣእ ወልደ እጓለ እመሕያው እሙታን፡-የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሳ ድረስ በዚህ በደብረ ታቦር ያያችሁትንና የሰማችሁትን ምስጢር ሁሉ ለማንም እንዳትናገሩ"ብሎ አዘዛቸው፡፡ ምክንያቱም ከውዳሴ ከንቱ ለመራቅና መከራ መስቀልን ወደ ኋላ አድርጎ የክብርን ነገር አስቀድሞ መናገር አይገባምና፡፡/ወንጌል ቅዱስ ንባቡና ትርጓሜው፡ ተፈሪ መኮንን ማተሚያ ቤት፡ 1916ዓ.ም፡ አዲስ አበባ፡ ገጽ ከ129-132/፡፡

አንድም፡- "ደብረ ታቦር"የቤተክርሰቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጸው በአማናዊት ደብረ ታቦር በቤተክርስቲያንም የምስጢረ ሥላሴን ትምህርት ይተነተናል፤ ይተረጉማልና፡፡ በደብረ ታቦር ጌትነቱን እንደ ገለጸ በአማናዊት ደብረ ታቦር በቤተክርስቲያንም ዘወትር በሚጸለየው ጸሎት ሕብስቱንና ወይኑን ወደ አማናዊ ሥጋና ደመ መለኮት በግብረ መንፈስ ቅዱስ ይለወጥበታልና፡፡

አንድም፡- "የደብረ ታቦር ተራራ"የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት፡፡ ደብረ ታቦር ተራራ ረዥም /572ሜ/ከመሆኑ የተነሳ ወደ ጫፍ ለመውጣት ብዙ ድካምና መከራ ይጠይቃል መንግስተ ሰማያትም ብዙ ምድራዊ /ሥጋዊ/መከራና ስቃይ ታግሰው ሲጸኑ የምትገኝ /የምትወረስ/ጸጋ እግዚአብሔር በመሆኗ፤ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያትም "እስመ በብዙኀ ፃማ ሀለወነ ንባእ ለመንግስተ እግዚአብሔር፡-ወደ እግዚአብሔር መንግስት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል" /ሐዋ. 14፡21-22/ በማለት አስተምረውናልና በዚህ ትመሰላለች፡፡

ደብረ ታቦር ከዚህም በላይ በሆነ ምስጢራዊ ረቂቅ የትርጓሜ ስልት በመመሰል በብዙ ሕብረ ምሳሌ የቤተክርስቲያናችን ጠበብት ሊቃውንት በቃላቸውም ሆነ በመጻሕፍቶቻቸው ይተረጉሙታል፡፡

በመሆኑም ለእኛ ለክርስቲያኖች ቅዱስ ጴጥሮስ "ለእኛ በዚህ መኖር መልካም ነው"እንዳለው በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሆነን የቤተክርስቲያናችን ሕግና ሥርዓት አክብረን፣ በምግባር በትሩፋት አጊጠን፣ ሕገ ተፋቅሮን አስቀድመን መኖር.... በሥጋዊ ዓይን መከራ ወይም ድካም መስሎ ቢታየንም መፍጻሜውን ግን ዘለአለማዊ ሕይወት ስለሆነ በቤቱ ፀንተን እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ መኖር መንፈሳዊ ግዴታችን መሆኑ ማወቅ መንፈሳዊ ጥበብ መሆኑ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡

ሥጋችን በሚያልፍና በሚረግፍ ጊዜያዊ የደስታ ምንጭ በሆነ የሥጋ ሥራ /ያልተፈቀደ የኃጢአት ሥራ/ይደሰት ይሆናል፡፡ ሆኖም ሥጋ በራሱ እንኳ ቢሆን ይህን ሕይወት ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ ስለማይሆን ይኸው የሚያስደስት የመሰለን ሥራ ተመልሶ የሕሊና ፀፀትና ቁጭት በሕሊናችን ፈጥሮ ኃጢአቱ ከፈጸምን ከጥቂት ጊዜ በኋላ የደስታው መልክ ይለወጣል፡፡ የሥጋ ፈቃዳችንን ገድለን ፈቃደ ነፍሳችን ተከትለን በሃይማኖታችን ፀንተን በጾምና በጸሎት ተወስነን፣ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ተቀብለን፣ በምግባረ ሃይማኖት የኖርን እንደሆነ ደግሞ ከወጣኒነት /ከጀማሪነት/ ወደ ማዕከላዊነት ከዚያም ወደ ፍጹምነት የሚያደርስ ፍኖተ ቅዱሳን የቅድሳን መንገድ መጓዝ ስንጀምር ፍጹም የሆነ ዘለአለማዊ ደስታ ገንዘብ እያደረግን ስንሄድ መንፈሳውያን ጸጋዎች ይበዙልናል፤ በዚህም የድኅነት መንገድ ጸንተን ከኖርን የዘለአለማዊ ሕይወት የመንግስተ ሰማያት ወራሾች እንሆናለን፡፡ ደስታችንም ፍጹም ዘለአለማዊ ይሆናል፡፡

በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር ቢኖረንም እግዚአብሔር ውስጣችን ላይ ከሌለ ምንም እንደሌለን ማወቅ አለብን፡፡ ለዚህ ጥሩ መምህራችን ቅዱስ ዳዊት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠው፣ እንደልቡ የሚወደው ትልቅ ሰው ሲሆን እግዚአብሔር የሰጠው ብዙ ሃብትና ንብረት እንዲሁም ክብር ተመክቶ ሳይታበይ ይህንን ሁሉ የዓለም ነገር ከንቱ ኃላፊና ረጋፊ መሆኑን አውቆ "ይኄይሰኒ ሕገ አፉከ እምአእላፈ ወርቅ ወብሩር" ከብዙ ወርቅና ብር ይልቅ ለእኔ የአንተ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል /መዝ......./ በማለት የተናገረው ምስክር ነው፡፡

በመጨረሻም በሀገረ ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር የምንኖር የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልጆች ሁላችንም ይህንን ዓመታዊ ታላቅ በዓላችን የሆነ "የደብረ ታቦር በዓል" ስናከብር ከልብ በሆነ መንፈሳዊ ፍቅር ተሳስበን፣ አንድነታችንን አጽንተን፣ ሃይማኖታችንን አክብረን፣ በጾምና በጸሎት በሱባዔ ሆነን.... የመታዘዝ ፍሬ በረከት ገንዘብ አድርገን መሆን ይገባናል፡፡ በዓሉ መንፈሳዊ በረከት የምናገኝበት፣ ኃጢአታችንን የምንናዘዝበት፤ ሥጋሁ ወደሙ የምንቀበልበት፤ ለሚመጣውም ሕይወት ተስፋችን የበለጠ የምናጸናብት ያድርግልን፡፡

አሜን!

በበዓለ ደብረ ታቦር የሚነበቡ ምንባባትና ምስባክ

የደብረ ታቦር የሌሊት ምስባከ መዝ. 68፡15-16

ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል

ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉዓን

ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኃድር ውስቴቱ 

ትርጉም

የጸና ተራራ የለመለመ ተራራ
የጸኑ ተራሮች ለምን ይነሣሉ
የወደደው ተራራ እግዚአብሔር በውስጡ ያድራል

የሌሊት ወንጌል ምንባብ

ሉቃ. ምዕ. 9፡28-35

የደብረ ታቦር የቅዳሴ ምንባባት

ዕብ.ምዕ.11፡23-30
2ጴጥ. ምዕ. 1፡15-ፍፃሜ ምዕራፍ
ግብ. ሐዋ. ምዕ. 7፡44-51

ምስባክ ዘቅዳሴ

ታቦር ወኤርምንዔም በስመ ዘአከ ይትፌስሑ
ወይስብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኃይል ....... (መዝ. 89፡12)"

ትርጉም

ታቦርና ኤርምንኤም በአንተ ስም ደስ ይላቸዋል
ስምህንም ያመሰግናሉ
ክንድህ ኃይል ከማድረግ ተራ ተገልጦላቸው (መዝ. 89፡12)

ወንጌል ዘቅዳሴ

ወን. ዘማቴ. ምዕ. 17፡1-8

የደብረ ታቦር ቅዳሴ

ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም አው ቅዳሴ ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ /መጽሐፈ ግጻዌ፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት
ጉባዔ የተዘጋጀ፣ ትንሣኤ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት፡ 1977ዓ.ም፡ አዲስ አበባ ገጽ 454/

አስረጅ መጻሕፍት

 • ወንጌል ቅዱስ ንባቡና ትርጓሜው፡ ተፈሪ መኮንን ማተሚያ ቤት፡ 1916ዓ.ም፡ አዲስ አበባ
 • አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፡ መጽሐፈ ስዋስወ ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡ 1948ዓ.ም፡ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡ አዲስ አበባ
 • የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
 • ማኅሌተ ጽጌ
 • መጽሐፈ ግጻዌ፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ያን የሊቃውንት ጉባዔ የተዘጋጀ፡ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፡ 1977ዓ.ም፡ አዲስ አበባ
 • Anthony M. Coniaris, This is my beloved Son LISTENED To HIM volume-1, light and life publishing company, Minneaplois, Minnesota 55426-0421, 1988

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
ይትአኮት ወይሰባሕ ስሙ ለእግዚአብሔር አምላክነ
ወትረ በኩሉ ጊዜ ሰዓት

View Event →
ጾመ ፍልሰታ - ከ ሰኞ ነሐሴ ፩ እስከ ሰኞ ነሐሴ ፲፭
Aug
7
to Aug 21

ጾመ ፍልሰታ - ከ ሰኞ ነሐሴ ፩ እስከ ሰኞ ነሐሴ ፲፭

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS

“ፍልሰታ” የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት ይነገራል።

ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሣቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው። ፍትሐ ነገስትአንቀጽ፲፭

ሃይማኖታዊ መሠረት

እመቤታችን ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄም እና ከእናቷ ከቅድስት ሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በአድባረ በሊባኖስ ተወልዳለች። “እምሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች “እንደተባለ ። እመቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ ዐሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ ዐሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።

ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ና ሲያውኩን ይኖራሉ: አሁን ደግሞ እሷም ተነሣች፣ ዐረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን በእሳት እናቃጥላት ብለው ተነሱ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው መልአክ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡ የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በዐረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በዐሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ ዐሳረፉት ። በሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰዱቃውያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ሥርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፡፡ ሊያስተምር ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሣኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እነዚያ ትንሣኤየን ዕርገቴንም አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡

ትንሣኤና ዕርገቷ

ከርሱ በቀር ማንንም ትንሣኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም (ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን ) መግነዟን ሰጥታው ዐረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት ዕኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም » እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ጴጥሮስም አንተ እንጂ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም አንተ እየተጠራጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው፡፡ እርሱም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሄዶ መቃበሩን ቢከፍተው አጣት ደንግጾ ቆመ «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው » ሁኔታውንም ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው ሰጣቸውም ። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደ የአህጉረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።

በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ዕርገትሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት ፤ጥንታዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።

የእመቤታችን ትንሣኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ውኃፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ « ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምእመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።

ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ …ዉበቴ»” የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ « ወትቀውም ንግስት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኍብርት ፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንደ ዐረገ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን ዕረፍቷን ትንሣኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።

ጾሙን አጋንንትን ድል የምንነሳበት እናየበረከት ያድርግልን !
ምንጭ ÷ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘእሑድ

View Event →
የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል (ሰኔ ሚካኤል)
Jun
19
11:30 AM11:30

የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል (ሰኔ ሚካኤል)

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS

የሰኔ ቅዱስ ሚካኤል ድርሳን

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን በባሕርይ በህልውና አንድ አምላክ ብለን አምነን ሰኔ በባተ በዓሥራ ሁለት ቀን የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ እንዲከበር እንናገራለን ልመናው አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

እግዚአብሔርን እጅግ አድርጐ የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር።

ለዚህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውም ርኅራኄ የሌለው በሱም ላይ ጥላቻ ያደረበት በለጸጋ ጐረቤት ነበረው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር።

ይህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውዬ በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ።

ሚስቱንም ጠርቶ በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመ መፅወት ቸል አትበይ የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው አላት በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር።

ይህም ሰው በሰላም ዓረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ።

ከዚህም በኋላ ሚስቱ የመውለጃዋ ጊዜ ተቃርቦ ነበርና ምጥ ይዟት በታላቅ ጭንቅ ላይ እንዳለች አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ሆይ በኔ ላይ ይቅርታን አውርድ ከዝህ ከደረሰብኝም ጭንቅ ይገላግለኝ ዘንድ ስለኔ እግዚአብሔርን ለምንልኝ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ባለሟልነት ተሰጥቶሃልና እያለች ለመነች።

ይህንንም በምትልበት ጊዜ ያለችበት ቤት በብርሃን ተመላ ከጭንቋም ዳነችና መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች።

የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለፀጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል አለ።

ያን ጊዜ ያ ባለፀጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ኅዘን ተነካ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።

ብላቴናውም ዓሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት በዚህን ጊዜ እምነት የጐደለው ያ ባለ ፀጋ አንቺ ችግረኛ ስለሆንሽ ይላከኝ ያገለግለኝ ዘንድ ልጅሽን ስጭኝና ምግቡንና ልብሱን ምንም ሳላጐድል ተንከባክቤ አኖረዋለው ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለው አላት።

ይህንንም ባላት ጊዜ ስለ ችግሯ በጣም በመደሰት ልጅዋን ሰጠችውና ሃያውን ወቄት ወርቅ ተቀበለች ብላቴናውንም በወሰደ ጊዜ እንግዲህ ሃሳቤ ሁሉ ዛሬ ተፈጸመልኝ እያለ በጣም ደስታ ተሰማው ከዚህ በኋላ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ (ከቶ) በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው።

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።

በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣና ወደ ቤቱ ወሰደው።

እቤቱም በደረሰ ጊዜ ይህን ሣጥን በምን እከፍተዋለሁ እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ተመልሶ ወደ ባሕሩ ይሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አሳሰበው በሄደም ጊዜ አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘ።

ያ በግ ጠባቂ ዓሣ አጥማጁን በኔ ስም መረብህን ወደ በሕር ጣልና የተሠገረው ዓሣ ለኔ ይሆናል ዋጋውን ግን እከፍልሃለው አለው ዓሣ አሥጋሪውም እንደ ተነጋገሩት መረብን ከባሕር ቢጥል ታላቅ ዓሣ ተያዘና ለሰውየው ሰጥቶት ዋጋውን ተቀበለ።

እሱም ያን ዓሣ ከቤተሰቦቹ ጋር ጠብሶ ይበላ ዘንድ በችኮላ ወደ ቤቱ ሄደና ያሣውን ሆድ ቢሰነጥቀው የዚያን የሣጥን ቁልፍ መክፈቻ አገኘ በዚያን ጊዜ ይህ መክፈቻ የዚህ ሣጥን ቁልፍ መክፈቻ መሆን አለበት ሲል አሰበና ቁልፉን ለመክፈት ቢሞክር ወለል ብሎ ተከፈተ። በዚህም እየተደነቀ ሳለ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው።

ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን ባሕራን ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዓሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው።

ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ፀጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ።

በግ ጠባቂውንም ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው ኪራዩንም እከፍልሃለው ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው።

ባለፀጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ልጅህ ነውን ብሎ ጠየቀው።

በግ ጠባቂውም አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው አለው።

ባለፀጋውም ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ ይገድለውም ዘንድ ፈልጐ በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም አወቀ።

በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሃሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ዕገሊት ወደ ምትባል ሀገር ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ አለው።

ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ ሲል ጠየቀው ልጁም እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ አለው።

ከዚህም በኋላ ያ ባለ ፀጋ ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወዳንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ የሚልጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ እንዲሁም በሹሙና በሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።

እሱም መልእክቱን ለማድረስ በሚጓዝበት ጊዜ ከቦታው ለመድረስ ያንዲት ቀን መንገድ ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉስ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው ባሕራንም ከአንድ ባለፀጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እሱን ለምድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ አለው።

ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ ባለው ጊዜ ከግርማው የተነሳ ፈርቶ ሰጠው መልአኩም ደብዳቤው ላይ የተጻፈውን መልእክተ ሞት ደምስሶ ከኔ ከባለፀጋ ዕገሌ የተጻፈ ይልና ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምት ባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና።

በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በኔና ባንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ የሚል ጽሑፍ ጽፎ ሰጠውና እንግዲህ ወደ ባለ ፀጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ ነገሩ እንዳይገለጽብህ ከኔ ጋር መገናኘታችንንና የመልእክቱን ጽሑፍ እንደለወጥኩልህ ለማንም አትንገር ሲል አስጠነቀቀው ባሕራንም እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።

ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ከአረጋገጠ በኋላ እግዚአብሔር እንዳዘዘው በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለፀጋውን ልጅ በተክሊል አጋባው የሠርጉንም በዓል እስከ ዐርባ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ።

ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለፀጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው ሲል ጠየቀ ሰዎቹም ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታሉ።

እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ዐርባ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል አሉት።

ያም ባለፀጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት።

ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር።

በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ።

ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቆጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።

View Event →
የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል (ሰኔ ሚካኤል)
Jun
18
6:00 AM06:00

የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል (ሰኔ ሚካኤል)

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS

የሰኔ ቅዱስ ሚካኤል ድርሳን

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን በባሕርይ በህልውና አንድ አምላክ ብለን አምነን ሰኔ በባተ በዓሥራ ሁለት ቀን የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ እንዲከበር እንናገራለን ልመናው አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

እግዚአብሔርን እጅግ አድርጐ የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር።

ለዚህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውም ርኅራኄ የሌለው በሱም ላይ ጥላቻ ያደረበት በለጸጋ ጐረቤት ነበረው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር።

ይህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውዬ በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ።

ሚስቱንም ጠርቶ በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመ መፅወት ቸል አትበይ የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው አላት በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር።

ይህም ሰው በሰላም ዓረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ።

ከዚህም በኋላ ሚስቱ የመውለጃዋ ጊዜ ተቃርቦ ነበርና ምጥ ይዟት በታላቅ ጭንቅ ላይ እንዳለች አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ሆይ በኔ ላይ ይቅርታን አውርድ ከዝህ ከደረሰብኝም ጭንቅ ይገላግለኝ ዘንድ ስለኔ እግዚአብሔርን ለምንልኝ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ባለሟልነት ተሰጥቶሃልና እያለች ለመነች።

ይህንንም በምትልበት ጊዜ ያለችበት ቤት በብርሃን ተመላ ከጭንቋም ዳነችና መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች።

የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለፀጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል አለ።

ያን ጊዜ ያ ባለፀጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ኅዘን ተነካ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።

ብላቴናውም ዓሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት በዚህን ጊዜ እምነት የጐደለው ያ ባለ ፀጋ አንቺ ችግረኛ ስለሆንሽ ይላከኝ ያገለግለኝ ዘንድ ልጅሽን ስጭኝና ምግቡንና ልብሱን ምንም ሳላጐድል ተንከባክቤ አኖረዋለው ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለው አላት።

ይህንንም ባላት ጊዜ ስለ ችግሯ በጣም በመደሰት ልጅዋን ሰጠችውና ሃያውን ወቄት ወርቅ ተቀበለች ብላቴናውንም በወሰደ ጊዜ እንግዲህ ሃሳቤ ሁሉ ዛሬ ተፈጸመልኝ እያለ በጣም ደስታ ተሰማው ከዚህ በኋላ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ (ከቶ) በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው።

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።

በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣና ወደ ቤቱ ወሰደው።

እቤቱም በደረሰ ጊዜ ይህን ሣጥን በምን እከፍተዋለሁ እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ተመልሶ ወደ ባሕሩ ይሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አሳሰበው በሄደም ጊዜ አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘ።

ያ በግ ጠባቂ ዓሣ አጥማጁን በኔ ስም መረብህን ወደ በሕር ጣልና የተሠገረው ዓሣ ለኔ ይሆናል ዋጋውን ግን እከፍልሃለው አለው ዓሣ አሥጋሪውም እንደ ተነጋገሩት መረብን ከባሕር ቢጥል ታላቅ ዓሣ ተያዘና ለሰውየው ሰጥቶት ዋጋውን ተቀበለ።

እሱም ያን ዓሣ ከቤተሰቦቹ ጋር ጠብሶ ይበላ ዘንድ በችኮላ ወደ ቤቱ ሄደና ያሣውን ሆድ ቢሰነጥቀው የዚያን የሣጥን ቁልፍ መክፈቻ አገኘ በዚያን ጊዜ ይህ መክፈቻ የዚህ ሣጥን ቁልፍ መክፈቻ መሆን አለበት ሲል አሰበና ቁልፉን ለመክፈት ቢሞክር ወለል ብሎ ተከፈተ። በዚህም እየተደነቀ ሳለ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው።

ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን ባሕራን ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዓሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው።

ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ፀጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ።

በግ ጠባቂውንም ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው ኪራዩንም እከፍልሃለው ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው።

ባለፀጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ልጅህ ነውን ብሎ ጠየቀው።

በግ ጠባቂውም አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው አለው።

ባለፀጋውም ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ ይገድለውም ዘንድ ፈልጐ በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም አወቀ።

በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሃሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ዕገሊት ወደ ምትባል ሀገር ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ አለው።

ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ ሲል ጠየቀው ልጁም እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ አለው።

ከዚህም በኋላ ያ ባለ ፀጋ ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወዳንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ የሚልጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ እንዲሁም በሹሙና በሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።

እሱም መልእክቱን ለማድረስ በሚጓዝበት ጊዜ ከቦታው ለመድረስ ያንዲት ቀን መንገድ ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉስ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው ባሕራንም ከአንድ ባለፀጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እሱን ለምድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ አለው።

ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ ባለው ጊዜ ከግርማው የተነሳ ፈርቶ ሰጠው መልአኩም ደብዳቤው ላይ የተጻፈውን መልእክተ ሞት ደምስሶ ከኔ ከባለፀጋ ዕገሌ የተጻፈ ይልና ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምት ባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና።

በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በኔና ባንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ የሚል ጽሑፍ ጽፎ ሰጠውና እንግዲህ ወደ ባለ ፀጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ ነገሩ እንዳይገለጽብህ ከኔ ጋር መገናኘታችንንና የመልእክቱን ጽሑፍ እንደለወጥኩልህ ለማንም አትንገር ሲል አስጠነቀቀው ባሕራንም እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።

ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ከአረጋገጠ በኋላ እግዚአብሔር እንዳዘዘው በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለፀጋውን ልጅ በተክሊል አጋባው የሠርጉንም በዓል እስከ ዐርባ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ።

ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለፀጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው ሲል ጠየቀ ሰዎቹም ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታሉ።

እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ዐርባ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል አሉት።

ያም ባለፀጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት።

ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር።

በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ።

ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቆጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።

View Event →
የግንቦት ማርያም
May
29
6:00 PM18:00

የግንቦት ማርያም

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS
የግንቦት ማርያም

ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት

ግንቦት ሃያ አንድ

፡- በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ሰለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ፡፡

፡- በዚችም ዕለት የነቢዮ አምድና የመርደላ መታሳቢያቸው ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘለዓለሙ ትኑር አሜን፡፡

 

View Event →
May
25
8:00 AM08:00

በዓለ ዕርገት (ግንቦት ፲፯ ፳፻፱ ዓ.ም.)

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS
The Feast of the Ascension of our Lord God and Savior Jesus Christ is one of the nine great feasts of the Church in the liturgical calendar, and commemorates each year the bodily Ascension of Jesus into Heaven. Ascension Day is always celebrated on a Thursday, the fortieth day after Easter day (Acts 1:3). The story of the Ascension of our Lord is stated in the book of the Acts of the Apostles 1:3-11. It is also mentioned in the Gospels of Mark (16:19) and Luke (24:50-53). In His last stay on earth, Jesus Christ was appeared, forty days after His Resurrection from the dead and commanded to His disciples not to depart from Jerusalem, but to wait for the "Promise of the Father". He stated, "You shall be baptized with the Holy Spirit not many days from now" (Acts 1:5). After Jesus gave these instructions, He led the disciples to the Mount of Olives. Then, He ordered them to be His witnesses "In Jerusalem, and in all Judea and Samaria, and to the end of the earth" (Acts 1:8). As the disciples watched, Jesus lifted up His hands, blessed them, and then was taken up out of their sight (Luke 24:51; Acts 1:9). Then they worshiped Him and returned to Jerusalem with great joy. And they stayed continually at the temple, praising God. Then two angels appeared to them and asked them why they were gazing into heaven. Then one of the angels said, "This same Jesus, which is taken up from you into heaven, shall so come in like manner as you have seen Him going into heaven" (Acts 1:11). The Ascension of Jesus Christ was vital in a chain of the fulfillment of the prophecy of the Old and New Testament times (Psalms 110:1; Matthew 26:64; John 6:62; John 7:33; John 14:28; John 16:5; John 20:17). A thousand years before the Savior’s birth, David prophesied the ascension of Jesus when he announced the Lord’s enthronement at the Father’s right hand (Psalm 110:1). The ascension of Christ into heaven endorses contrary to Jewish expectations, the coming of Lord to this world was not to overthrow Rome, and establish an earthly, political administration as stated in different parts of the Bible, (John 6:15; 18:36; Acts 1:6). In contra to the Jewish expectations the ascension of Christ approves the end of His redemptive work and the end of His public ministry of words and works (John 17:4-11; Heb. 1:3; 10:12)  Glory be to our Lord God and Savior Jesus Christ!

The Feast of the Ascension of our Lord God and Savior Jesus Christ is one of the nine great feasts of the Church in the liturgical calendar, and commemorates each year the bodily Ascension of Jesus into Heaven. Ascension Day is always celebrated on a Thursday, the fortieth day after Easter day (Acts 1:3). The story of the Ascension of our Lord is stated in the book of the Acts of the Apostles 1:3-11. It is also mentioned in the Gospels of Mark (16:19) and Luke (24:50-53).

In His last stay on earth, Jesus Christ was appeared, forty days after His Resurrection from the dead and commanded to His disciples not to depart from Jerusalem, but to wait for the "Promise of the Father". He stated, "You shall be baptized with the Holy Spirit not many days from now" (Acts 1:5).

After Jesus gave these instructions, He led the disciples to the Mount of Olives. Then, He ordered them to be His witnesses "In Jerusalem, and in all Judea and Samaria, and to the end of the earth" (Acts 1:8). As the disciples watched, Jesus lifted up His hands, blessed them, and then was taken up out of their sight (Luke 24:51; Acts 1:9).

Then they worshiped Him and returned to Jerusalem with great joy. And they stayed continually at the temple, praising God. Then two angels appeared to them and asked them why they were gazing into heaven. Then one of the angels said, "This same Jesus, which is taken up from you into heaven, shall so come in like manner as you have seen Him going into heaven" (Acts 1:11).

The Ascension of Jesus Christ was vital in a chain of the fulfillment of the prophecy of the Old and New Testament times (Psalms 110:1; Matthew 26:64; John 6:62; John 7:33; John 14:28; John 16:5; John 20:17). A thousand years before the Savior’s birth, David prophesied the ascension of Jesus when he announced the Lord’s enthronement at the Father’s right hand (Psalm 110:1).

The ascension of Christ into heaven endorses contrary to Jewish expectations, the coming of Lord to this world was not to overthrow Rome, and establish an earthly, political administration as stated in different parts of the Bible, (John 6:15; 18:36; Acts 1:6). In contra to the Jewish expectations the ascension of Christ approves the end of His redemptive work and the end of His public ministry of words and works (John 17:4-11; Heb. 1:3; 10:12)

Glory be to our Lord God and Savior Jesus Christ!

View Event →
Apr
15
to Apr 16

በዓለ ትንሣኤ

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለእኛ ድኅነት እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፉ ያስረዳል። ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰፊው አብራርቶልናል። “የሰው ልጅ በራሱ ጥፋት በሞት ጥላ ሥር ቢወድቅም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በሞቱ ደምስሶ ለሚያምኑበት ሕይወትን ድኅነትን አውጇል። “አሁን ግን ክርስቶስ ለአንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተለይቶ ከሞት ተነስቶአል።” (፩ኛ ቆሮ.፲፭፥፳-፳፩) ሐዋርያውና ወንጌላዊው ማቴዎስ እንደጻፈው ኢየሱስ እኛን ከድካማችን ሁሉ ለማሳረፍ በእርሱም ዘንድ እረፍትን እንድናገኝ በቃሉ እንደጋበዘን ሲያስረዳን “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ” (ማቴ. ፲፩፥፳፰) እያለ ጥሪውን ያስተላልፋል። ስለዚህ ቤተክርስቲያናችንም ይህንን ቅዱስ ቃል መርሆ በማድረግ ወደ እግዚአብሔር ቤት ምዕመናንን በየጊዜው ትጋብዛለች። አሁንም እንኳን ለብርሃነ ትንሣዔው በሰላምና በሕይወት አደረሳችሁ እያልን እርስዎ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣዔና ሕይወት ተካፋይ እንዲሆኑ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ስም ጥሪ እናቀርባለን። ይህም ጥሪ የእግዚአብሔር እንጂ ከሰው እንዳይደለ ክፍ ብሎ ተገልጿል። የእግዚአብሔርንም ጥሪ የተቀበሉ በእርሱ የሚመሩ በደስታ ይኖራሉ። የፈለጉት ሁሉ ይፈጸምላቸዋል። ይህንንም ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ሲል ያረጋግጣል። “ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ቢኖር ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል። ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን።” (የያዕቆብ መልዕክት ፩፥፭-፯) ስለሆነም በዓሉ የበረከት የሰላምንና ፍቅርን በዓል ይሁንልዎ። ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ። “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል። ሞት በሰው በኩል ስለመጣ ትንሣዔ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።” (፩ኛ ቆሮ.፲፭፥፳-፳፩) የትንሣዔ ፕሮግራም ቅዳሜ ሚያዚያ ፯ ቀን ፪ሺህ፱ ዓ.ም. ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት እስከ ሌሊቱ ፯ ሰዓት ተኩል ድረስ ያካሄዳል። ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት    የወንጌል ትምህርት። ከምሽቱ ፪ ሰዓት ፴    የመክፈቻ ጸሎትና ማሕሌት። ከምሽቱ ፫ ሰዓት ተኩል     ጸሎተ ወንጌል ምስባክ። ዘተንሣዔ ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘነቃህ እምንዋም ወከመ ኅያል ወኅዳገ ወይን ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ። እግዚአብሔርም ከአንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ። የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው። ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ። መዝሙር ፸፰ ፥ ፷፭ - ፷፮ የማቴዎስ ወንጌል ፳፰ ፥ ፩ - ፲፭  ምልጣን (አንገርጋሪ) እስመ ለዓለም በዚህ ጊዜ ምዕመናኑ ጧፍ ያበራሉ የደብሩ ታዳጊ መዘምራን “ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ “ ወረብ ያቀርባሉ። ከምሽቱ ፬ ሰዓት ከሩብ   ኪዳን ከምሽቱ ፬ ሰዓት ተኩል     ቅዳሴ ይጀመራል የዕለቱ ንባብ፤      ፩ ቆሮንቶስ ፲፭ ፥ ፳ - ፵፩                    ፩ ጴጥሮስ ፩ ፥ ፩ - ፲፫                    የሐዋርያት ሥራ ፪ ፥ ፳፪ - ፴፯ ምስባክ፤       መዝሙር ፸፰ ፥ ፷፭ - ፷፮ ወንጌል፤      የዮሐንስ ወንጌል ፳ ፥ ፩ - ፲፱ ከሌሊቱ ፯ ሰዓት ተኩል  ሲሆን ስርወተ ሕዝብ ይሆናል።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለእኛ ድኅነት እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፉ ያስረዳል። ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰፊው አብራርቶልናል። “የሰው ልጅ በራሱ ጥፋት በሞት ጥላ ሥር ቢወድቅም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በሞቱ ደምስሶ ለሚያምኑበት ሕይወትን ድኅነትን አውጇል። “አሁን ግን ክርስቶስ ለአንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተለይቶ ከሞት ተነስቶአል።” (፩ኛ ቆሮ.፲፭፥፳-፳፩) ሐዋርያውና ወንጌላዊው ማቴዎስ እንደጻፈው ኢየሱስ እኛን ከድካማችን ሁሉ ለማሳረፍ በእርሱም ዘንድ እረፍትን እንድናገኝ በቃሉ እንደጋበዘን ሲያስረዳን “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ” (ማቴ. ፲፩፥፳፰) እያለ ጥሪውን ያስተላልፋል። ስለዚህ ቤተክርስቲያናችንም ይህንን ቅዱስ ቃል መርሆ በማድረግ ወደ እግዚአብሔር ቤት ምዕመናንን በየጊዜው ትጋብዛለች። አሁንም እንኳን ለብርሃነ ትንሣዔው በሰላምና በሕይወት አደረሳችሁ እያልን እርስዎ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣዔና ሕይወት ተካፋይ እንዲሆኑ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ስም ጥሪ እናቀርባለን። ይህም ጥሪ የእግዚአብሔር እንጂ ከሰው እንዳይደለ ክፍ ብሎ ተገልጿል። የእግዚአብሔርንም ጥሪ የተቀበሉ በእርሱ የሚመሩ በደስታ ይኖራሉ። የፈለጉት ሁሉ ይፈጸምላቸዋል። ይህንንም ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ሲል ያረጋግጣል። “ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ቢኖር ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል። ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን።” (የያዕቆብ መልዕክት ፩፥፭-፯) ስለሆነም በዓሉ የበረከት የሰላምንና ፍቅርን በዓል ይሁንልዎ።

ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ
በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ።

“አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል። ሞት በሰው በኩል ስለመጣ ትንሣዔ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።” (፩ኛ ቆሮ.፲፭፥፳-፳፩)

የትንሣዔ ፕሮግራም ቅዳሜ ሚያዚያ ፯ ቀን ፪ሺህ፱ ዓ.ም. ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት እስከ ሌሊቱ ፯ ሰዓት ተኩል ድረስ ያካሄዳል።

ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት    የወንጌል ትምህርት።
ከምሽቱ ፪ ሰዓት ፴    የመክፈቻ ጸሎትና ማሕሌት።
ከምሽቱ ፫ ሰዓት ተኩል     ጸሎተ ወንጌል ምስባክ።

ዘተንሣዔ

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘነቃህ እምንዋም ወከመ ኅያል ወኅዳገ ወይን ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።

እግዚአብሔርም ከአንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ። የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው። ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ።

መዝሙር ፸፰ ፥ ፷፭ - ፷፮
የማቴዎስ ወንጌል ፳፰ ፥ ፩ - ፲፭ 

ምልጣን (አንገርጋሪ) እስመ ለዓለም

በዚህ ጊዜ ምዕመናኑ ጧፍ ያበራሉ

የደብሩ ታዳጊ መዘምራን “ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ “ ወረብ ያቀርባሉ።

ከምሽቱ ፬ ሰዓት ከሩብ   ኪዳን
ከምሽቱ ፬ ሰዓት ተኩል     ቅዳሴ ይጀመራል

የዕለቱ ንባብ፤      ፩ ቆሮንቶስ ፲፭ ፥ ፳ - ፵፩
                   ፩ ጴጥሮስ ፩ ፥ ፩ - ፲፫
                   የሐዋርያት ሥራ ፪ ፥ ፳፪ - ፴፯

ምስባክ፤       መዝሙር ፸፰ ፥ ፷፭ - ፷፮

ወንጌል፤      የዮሐንስ ወንጌል ፳ ፥ ፩ - ፲፱

ከሌሊቱ ፯ ሰዓት ተኩል  ሲሆን ስርወተ ሕዝብ ይሆናል።

View Event →
Apr
14
7:00 AM07:00

ስቅለት ዓርብ

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS
ዕለተ ዐርብ  ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ  « አውቀውስ   ቢኾን   የክብርን   ጌታ   ባልሰቀሉት »  በማለት እንደ ተናገረው (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፲፰) ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ንጹሕና ጻድቅ የኾነውን ጌታ ያለበደሉና ያለጥፋቱ በሐሰት ወንጅለው የሰቀሉበት፤ ጌታችንም በፈቃዱ በመስቀል የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዅሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው (ማቴ. ፳፯፥፴፭-፸፭)፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ  ‹‹ ንጹሕ   ደም   አሳልፌ   በመስጠቴ   በድያለሁ››  አለ፡፡ እነርሱ ግን  ‹‹ እኛስ   ምን   አግዶን ?     አንተው   ተጠንቀቅ፤››  አሉ፡፡ ይሁዳም ብሩን በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው  ‹‹ የደም   ዋጋ   ነውና   ወደ   መባዕ   ልንጨምረው   አልተፈቀደም ፤››  አሉ፡፡ ተማክረውም ለእንግዶች መቃብር የሚኾን የሸክላ ሠሪ መሬት ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ ‹የደም መሬት› ተባለ (ማቴ. ፳፯፥፫-፱)፡፡ ዕለተ ዓርብ እኛ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት (ቁራኝነት) እንኖርበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመባትና ፍጹም ድኅነት ያገኘንባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ዅልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ የክርስቶስን ሕማሙን፣ ስቅለቱንና ሞቱን የምናስብበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት፤ የሕይወት መቅጫ አርማ ኾኖ ሳለ ለእኛ ግን የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት ዕለቱ ‹መልካሙ ዓርብ› በመባል ይታወቃል፡፡

ዕለተ ዐርብ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አውቀውስ ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» በማለት እንደ ተናገረው (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፲፰) ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ንጹሕና ጻድቅ የኾነውን ጌታ ያለበደሉና ያለጥፋቱ በሐሰት ወንጅለው የሰቀሉበት፤ ጌታችንም በፈቃዱ በመስቀል የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዅሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው (ማቴ. ፳፯፥፴፭-፸፭)፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ‹‹ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ›› አለ፡፡ እነርሱ ግን ‹‹እኛስ ምን አግዶን?  አንተው ተጠንቀቅ፤›› አሉ፡፡ ይሁዳም ብሩን በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው ‹‹የደም ዋጋ ነውና ወደ መባዕ ልንጨምረው አልተፈቀደም፤›› አሉ፡፡ ተማክረውም ለእንግዶች መቃብር የሚኾን የሸክላ ሠሪ መሬት ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ ‹የደም መሬት› ተባለ (ማቴ. ፳፯፥፫-፱)፡፡

ዕለተ ዓርብ እኛ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት (ቁራኝነት) እንኖርበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመባትና ፍጹም ድኅነት ያገኘንባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ዅልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ የክርስቶስን ሕማሙን፣ ስቅለቱንና ሞቱን የምናስብበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት፤ የሕይወት መቅጫ አርማ ኾኖ ሳለ ለእኛ ግን የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት ዕለቱ ‹መልካሙ ዓርብ› በመባል ይታወቃል፡፡

View Event →
Apr
13
10:00 AM10:00

ጸሎተ ሀሙስ - ኅፅበተ እግር

 • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል (map)
 • Google Calendar ICS
ጸሎተ ሀሙስ - ኅፅበተ እግር

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው፤ ፍጹም አምላክ መኾኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› በመባል ይታወቃል፡፡ ትሕትናንና ፍቅርን እንደዚሁም የአገልግሎትን ትርጕም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› በመባልም ይጠራል፡፡ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜም፡- «… ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?… እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስኾን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድይገባችኋል፤››  በማለት የእርሱን አርአያነት መከተል እንደሚገባ አስተምሯል (ዮሐ. ፲፫፥፲፪-፳)፡፡

ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ‹‹… ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱ ጠጡ፤›› በማለት ምሥጢረ ቍርባንን የመሠረተበት የጀመረበት ቀን በመኾኑ ‹የምሥጢር ቀን› ተብሎም ይጠራል (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱)፡፡ ይኸውም ምእመናን ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን፤ ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ አይሁድ ጌታችንን የያዙበት ቀን ስለ ኾነ በዚህ ዕለት በለኆሣሥ (ብዙ የድምፅ ጩኸት ሳይሰማ) የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ መላው ሕዝበ ክርስቲያን የሕጽበት፣ የምሥጢር፣ የጸሎት ቀን በተባለው በዚህ ዕለት በንስሐ ታጥበው፣ ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአጽንዖት ታስተምራለች፡፡

View Event →
Apr
9
5:00 AM05:00

በዓለ ሆሣዕና ነው: በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል።

https://youtu.be/cLD-wJBHuaI      |      https://youtu.be/hzm6mtz7cgc      |      https://youtu.be/XB5XH2TygR4

በዓለ ሆሣዕና

ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ሲኾን “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸሙት ጌታ በትሕትና በአህያና በውርንጫይቱ በትሕትና ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል፡፡ ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ናት፤ ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታም ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” በማለት እንደ ማዕምረ ኅቡአትነቱ (የተሰወረውን ዐዋቂነቱ) በመንደሯ ውስጥ ስለታሰሩት አህያና ውርንጫ አስቀድሞ ይነግራቸዋል፡፡

በተናቀች ግርግም በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ላምና አህያ ትንፋሻቸውን እንደገበሩለት፤ አኹንም በሰዎች በተናቀች አህያ በጌትነት ተቀምጦ እንዲመሰገንባት መርጧታል፡፡ ከዚያም “ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ጌታ ርሱ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም እንዲያመጡ አዟቸዋልና፤ አምጥተው “ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”፤ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ፤ ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ፡፡

ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማነ ሐዲስ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯል፡- 14ቱ በእግሩ መኼዱ የ10ሩ ቃላት 4ቱ የ4ቱ ኪዳናት ምሳሌ፡፡ 2ቱ በአህያዋ መጓዙ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ፤ 3ቱን በውርንጫዋ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን መዞሩ የ3ትነቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነበር፡፡ ክብር ይግባውና ጌታ ንጉሠ ነገሥት ሲኾን፤ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በፍርሀት በረአድ የሚሸከሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን በፍርሀት የሚያጥኑለት ርሱ በትሕትና የዋህ ኾኖ በተናቁት በአህያና በውርንጫይቱ ላይ ተቀመጠ፤ ይኽም የተናቁትን ሊያከብር እንደመጣና፤ በየዋሀን ምእመናን ልቡና እንደሚያድር ለማሳወቅ በነርሱ ተቀመጠ፤ በአህያ የተቀመጠ አባሮ እንደማይዝ ሸሽቶ እንደማያመልጥ ርሱም ካልፈለጉት እንደማይገኝ ከፈለጉት እንደማይታጣ በምስጢር አመለከታቸው፡፡

ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡- ስለዚኽ ነገር በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ “እነዚኽ እንስሳት መላውን የሰው ልጅ ይወክላሉ፡፡ ኹለቱም አህያ መኾናቸውም የሰው ልጅ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረውን አኳኋን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም አህያ በኦሪቱ ዘንድ ንጹሕ እንስሳ አይደለችም፤ ብዙ ክብደት ያላት የማትወደድ እንስሳ ናት፤ ዲዳ ናት፤ ደካማ ናት፡፡ ሰውም እንደተናገርን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት እንዲኽ ነበረ፡፡” በማለት አመስጥሯል፡፡

ሊቁ ቅ. ቄርሎስ ዘእስክንድርያም፡- “ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ጠቢብ አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ማሰብና ማሰላሰል የሚችል ፍጥረት አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ግን አታለለው፡፡ ምንም እንኳን ሰው በሥላሴ አምሳል ቢፈጠርም መልኩን አበላሸው፡፡ ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ተሳነው፡፡ ክፉው ሰይጣን ሰውን እንስሳ እስኪመስል ድረስ ክብሩን አዋረደው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት፡- “ሰውስ ክብሩን አላወቀም፤ የሚጠፉ እስሳትን መሰለ” ያለውም ስለዚኹ ነው /መዝ.49፡12/፡፡ በመኾኑም አህያይቱ ክብራቸውን አጥተው ተዋርደው የነበሩትን እስራኤል ዘሥጋን ትመስላለች፡፡ እስራኤል ከሕጉ ጥቂት ነገርን ያውቃሉ፡፡ ከነቢያትና ከቅዱሳንም ትንሽ ያውቃሉ፡፡ ከኹሉም በላይ ደግሞ ወደ አሚን የሚጠራቸውን ክርስቶስን አልታዘዙትም፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲላቸውም እንደምን እንደ አሕያይቱ በድንቁርና ተይዘው እንደነበረ ሲገልጥላቸው ነው፡፡ ውርንጫይቱ ደግሞ አሕዛብን ትወክላለች፡፡ ውርንጫ እኽልን ለመጫን እንደማታገለግል ኹሉ አሕዛብም ማኅደረ እግዚአብሔር ከመኾን ርቀው ነበርና፡፡” በማለት ገልጽዋል፡፡

ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡”
ሊቁ አምብሮስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑ ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል፡፡

ያን ጊዜ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ይኽንም ማድረጋቸው ስንኳን አንተ የተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባኽም ሲሉ ነበር፤ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር፡፡
ይኽም ዘንባባ ብዙ ምሳሌ ያለው ነው፤ ይኸውም በእስራኤል ያለው ሰሌን፣ ተምር፣ ዘይት ነበርና ያነን ቈርጠው አመስግነውታል፤ ይኽም ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኽም ሰሌን እሾኻማ እንደኾነ ትእምርተ ኀይል ትእምርተ መዊእ አለኽ ሲሉ ነው፤ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ እንደማያቃጥለው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
ዳግመኛም ከሰሌን ዝንጣፊ ጋር ተመሳሳይ ተምር ይዘዋል ይኽም ተምር ልዑል ነው አንተም ልዑለ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ፍሬው አንድ እንደኾነ አንተም ዋሕደ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፡፡ በእሾኽ የተከበበ ነው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
የዘይት ዛፍ ነው ቢሉ ዘይት ጽኑዕ እንደኾነ ጽኑዐ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ብሩህ ነው ብሩሀ ባሕርይ ነኽ በትምህርትኽም የሰውን ልቡናን ታበራለኽ ሲሉ፤ ዘይት መሥዋዕት እንደሚኾን መሥዋዕት ትኾናለኽ ሲሉ ነበር፡፡

“የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር” በማለት በአርያም መድኀኒት እንደኾነና እግዚአብሔር አብ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ መስክሮለት የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን የሚያድል መኾኑን ኹሉም መሰከሩለት፡፡

በእጅጉ የሚደንቀው የ40 ቀን የ80 ቀን ሕጻናት የፈጠራቸው ጌታ በአህያና በውርንጫ ተቀምጦ ባዩት ጊዜ በንጹሕ አንደበታቸው አንደታቸው ረቶላቸው ጌታን ዘንባባ በመያዝ ሲያመሰግኑ በእጅጉ ይደንቅ ነበር፤ ነገር ግን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት፤ ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? በማለት በሕጻናት እንደሚመሰገን የነርሱም ጌታ መኾኑን ከዳዊት መዝሙር በመጥቀስ ነገራቸው፡፡

ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሰለዚኽ ምስጢር ሲገልጸው ፡- “ፍቅርኅ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ዠርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደኅ፡፡ ብዙ ዓይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሠራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደደክ፡፡ በሰማይ ሠራዊት ሠረገላ ተቀምጠኅ ክብርኅን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጠኅ ወደ ሰማይ ሠራዊት መኼድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ያመሰግኑኻል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልኻል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድኽን ያነጥፉልኻል፤ በምድርም ደቀ መዛሙትኽ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድኽን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲኾን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከ መኾን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” በማለት አስተምሯል፡፡

የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ሕፃናትን ጨምሮ ዘንባባ ሰሌን በያዙት ኹሉ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትን ታላቁን በዓል ከኹሉም ዓለም አስበልጣ በታላቅ ክብር የምታከብርና የምታስተምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ይኸውም ታላቁ የምስጋና ዕለት ሊደርስ ሲቃረብ ስንዱዋ እመቤት አስቀድማ በቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የቊርባን ምስጋና “ቦአ ኀቤሃ እግዚአ አጋዕዝት ወመናፍስት እንዘ ይጼዐን ዕዋለ አድግ ትሑት…” (የአጋዕዝትና የመናፍስት ጌታ በተዋረደ አህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ ርሷ ገባ፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፡፡ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤልም ንጉሥ እግዚአብሔር ቡሩክ ነኽ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ኹሉ ጌትነቱን አሳየ፤ የሆሳዕናን ዑደት ለነርሱ ለደቀ መዛሙርቱ አሳየ፤ ቡርክ ርሱ በታላቅ ቃል እየጮኻችኊ ሆሣዕና በአርያም በሉ አላቸው፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ከዚኽ አስቀድሞ ያልተደረገ ከዚኽም በኋላ የማይደረግ ተአምራትንና መንክራትን አሳየ፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ከቤቱ መሠረት ሳይናወጥ ከልዑል መንበሩ ወርዶ ጸጋንና ኀይልን አሳየ፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ለኃጥኣን የዕንባ ምንጭ ሰጠ፤ የበደሉትን ያጸድቃቸው ዘንድ ያደፉትን ያነጻቸው ዘንድ የሳቱትን ይመልሳቸው ዘንድ፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ለዕውራን ዳግመኛ የማጠፋ ዓለም ሊቀበለው የማይቻለውን ብርሃንን ሰጣቸው ከኅሊና አስቀድሞ ያውቃል ከዐሳብም በፊት አስቀድሞ ይመረምራል የሚሰወረውም የለም) በማለት መድኀኒትነቱን ስትሰብክ፤ ካህናትና ምእመናንም በአንድ ድምፅ በዚያ ዘመን የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተመሰገነበት በዚኽ ልዩ ምስጋና “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ በመዘመር፤ ፈጣሪያቸው ክርስቶስን ያመሰግናሉ፡፡

ከዚያም በዋዜማው “በዕምርት ዕለት በዓልነ ንፉሑ ቀርነ በጽዮን ወስብኩ በደብረ መቅደስየ እስመ ይቤ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ሆሣዕና በአርያም ቡሩክ አንተ ንጉሠ እስራኤል” (በታወቀች በበዓላችን ዕለት በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በመቅደሴ ተራራም ስበኩ ይኽቺ ዕለት የእግዚአብሔር በዓል ናት፤ በአርያም መድኀኒት የተባልኽ የእስራኤል ንጉሥ አንተ ቡሩክ (መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የምታርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የምታድል) ነኽ) በማለት ልዩ ምስጋናዋን ዠምራ እስከ ሌሊቱ ድረስ በልዩ ምስጋና እየሰበከችው በኋላም ቤተ መቅደሱን በውርጫዋ ተቀምጦ እንደዞረ በአራቱ መኣዝን የጌትነቱ ወንጌል እየተነበበ፤ ካህናቱን ምእመናንም በእጃቸው የዘንባባ ዝንጣፊን ይዘው “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ያመሰግኑታል፡፡
 

View Event →