Contact Us

Use the form on the right to contact us.

You can edit the text in this area, and change where the contact form on the right submits to, by entering edit mode using the modes on the bottom right. 

(416) 781-4802

About Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
--------------------------------------------------------------

Ethiopia, the land of Judeo-Christianity, is one of the most ancient predominantly Christian countries of the world. It is marked with a fascinating history, unique civilization, culture and religious life. The Book of Genesis recounts: “And the name of the second river is Ghion: the same is it that compasses the whole land of Ethiopia” (Geneses 2:13). The Psalmist David also says: “Let Ethiopia hasten to stretch out her hands to God” (Psalms 68:31).

አጽዋማት እና በዓላት

Back to All Events

ስቅለት ዓርብ

  • በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል 84 Tycos Drive North York, ON, M6B 1V9 Canada (map)
ዕለተ ዐርብሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አውቀውስ ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» በማለት እንደ ተናገረው (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፲፰) ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ንጹሕና ጻድቅ የኾነውን ጌታ ያለበደሉና ያለጥፋቱ በሐሰት ወንጅለው የሰቀሉበት፤ ጌታችንም በፈቃዱ በመስቀል የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓ…

ዕለተ ዐርብ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አውቀውስ ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» በማለት እንደ ተናገረው (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፲፰) ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ንጹሕና ጻድቅ የኾነውን ጌታ ያለበደሉና ያለጥፋቱ በሐሰት ወንጅለው የሰቀሉበት፤ ጌታችንም በፈቃዱ በመስቀል የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዅሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው (ማቴ. ፳፯፥፴፭-፸፭)፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ‹‹ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ›› አለ፡፡ እነርሱ ግን ‹‹እኛስ ምን አግዶን?  አንተው ተጠንቀቅ፤›› አሉ፡፡ ይሁዳም ብሩን በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው ‹‹የደም ዋጋ ነውና ወደ መባዕ ልንጨምረው አልተፈቀደም፤›› አሉ፡፡ ተማክረውም ለእንግዶች መቃብር የሚኾን የሸክላ ሠሪ መሬት ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ ‹የደም መሬት› ተባለ (ማቴ. ፳፯፥፫-፱)፡፡

ዕለተ ዓርብ እኛ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት (ቁራኝነት) እንኖርበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመባትና ፍጹም ድኅነት ያገኘንባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ዅልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ የክርስቶስን ሕማሙን፣ ስቅለቱንና ሞቱን የምናስብበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት፤ የሕይወት መቅጫ አርማ ኾኖ ሳለ ለእኛ ግን የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት ዕለቱ ‹መልካሙ ዓርብ› በመባል ይታወቃል፡፡

Later Event: April 15
በዓለ ትንሣኤ