Contact Us

Use the form on the right to contact us.

You can edit the text in this area, and change where the contact form on the right submits to, by entering edit mode using the modes on the bottom right. 

(416) 781-4802

About Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
--------------------------------------------------------------

Ethiopia, the land of Judeo-Christianity, is one of the most ancient predominantly Christian countries of the world. It is marked with a fascinating history, unique civilization, culture and religious life. The Book of Genesis recounts: “And the name of the second river is Ghion: the same is it that compasses the whole land of Ethiopia” (Geneses 2:13). The Psalmist David also says: “Let Ethiopia hasten to stretch out her hands to God” (Psalms 68:31).

መጪ ክስተቶች


Apr
5
11:30 AM11:30

ጥንተ ስቅለት (በዓለ መድኃኔ ዓለም)

  • Ethiopian Orthodox Tewahedo Church - Menbere Berhan Kidest Mariam (St. Mary) Cathedral (map)
  • Google Calendar ICS
Annual Feast of the Saviour of the World (April 5, 2017)

ጥንተ ስቅለት- መጋቢት 27፣ 34 ዓ.ም.

የዛሬ አንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ዓመት በዕለተ ዓርብ መጋቢት 27 ቀን 34 ዓመተ ምሕረት (5534 ዓመተ ዓለም) የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው፡ ‹‹ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ›› (ማቴዎስ 27፡45) ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች፡፡ እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት፡፡ ሐዋርያጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ፤ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች፤ በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር፡፡ እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋር አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡ (1 ጴጥሮስ 3፡18-19)

እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ፣ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሡን ሰውቶ ያዳነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል፡፡

ለዘለዓለሙ የመስቀሉም በረከት በላያችን ይደር፤ አሜን፡፡

(የመጋቢት 27 ቀን ስንክሳር )

 

View Event →