Contact Us

Use the form on the right to contact us.

You can edit the text in this area, and change where the contact form on the right submits to, by entering edit mode using the modes on the bottom right. 

(416) 781-4802

About Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
--------------------------------------------------------------

Ethiopia, the land of Judeo-Christianity, is one of the most ancient predominantly Christian countries of the world. It is marked with a fascinating history, unique civilization, culture and religious life. The Book of Genesis recounts: “And the name of the second river is Ghion: the same is it that compasses the whole land of Ethiopia” (Geneses 2:13). The Psalmist David also says: “Let Ethiopia hasten to stretch out her hands to God” (Psalms 68:31).

Church Website - Homepage Image for Mobile Devices.PNG

ማንነታችን

እንኳን ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ድህረ ገፅ በሰላም መጡ።

        ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ, አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ

        ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ, አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ

 እ.ኤ.አ. በ1972 ዓ.ም. በካናዳ የሚገኙ የዌስት ኢንዲስና የካሪቢያን አገሮች በአብዛኛው የጃማይካ ተወላጆች ጥረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በምዕመናን ጉባኤነት ደረጃ (ሚሽን) ተመሠረተ፤ እ.ኤ.አ. በ1984 ዓ.ም.የዚህ ጉባኤ አባላቶች ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳን ከጃማይካ ወደ ቶሮንቶ እንዲመጡ አደረጉ፤ ይህ በመሆኑ ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ 425 ቫን ሮድ (425 Vaughan Road) በመባል በሚታወቀው መንገድ አንድ አነስ ያልች ቤት ተገዝቶ በካናዳ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን ተቋቋመ። ይህም ቤተ ክርስቲያን በቶሮንቶና በአካባቢው ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች ለሆኑ ኢትዮጵያዊያንንና የውጪ ዜጎችን ማገልገል ጀመረ። በዚያን ጊዜ የሚሰጠው አገልግሎት በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ነበር። የምዕመናኑ ቁጥር መጨመርና የቦታው ማነስ ምክንያት ሌላ ቤተ ክርስቲያን መጨመር ግድ ሆነ።

ስለዚህም 425 ቮን ሮድ ያለው የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች ምዕመናንን ሲገለገሉበት ሌላ በቅድስት ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. በ1991 ዓ.ም. ተመሠረተ። ይህ ቤተ ክርስቲያን ከ1991 ዓ.ም. እስከ  1996 ዓ.ም.  ማብቂያ ድረስ 40 ዌስትሙር ላንድ (40 Westmoreland Ave.) በሚገኝ  በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን በኪራይ መልክ እሑድ እሑድ የቅዳሴ ሥርዓትን ረቡዕ አርብና ቅዳሜ ምሽት ላይ የጸሎት አገልግሎት ለምዕመናኑ ሲሰጥ ቆየ።

ከዚህም በመቀጠል ለመጀመሪያ ጊዜ በካናዳ ምድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ንብረት በማፍራት በጥቅምት ወር 1996 ዓ.ም. የ80 ታይኮስ ድራቭ ላይ ያለውን ሕንፃ በመግዛት ወደ እዚህ ስፍራ ለመዛወር ዝግጅት ላይ እንዳለ ከርሱ ቀጥሎ የሚገኘው ህንፃ ደግሞ ለሽያጭ ስለቀረበ በጥር ወር 1997 ዓ.ም. ግዢውን አጠናቆ የሁለት ሕንፃዎች ባለቤት በመሆን የ80 ታይኮስን ለቢሮና ለመንፈሣዊና ለማሕበራዊ ኑሮ ዝግጅቶች የሚሆኑ አንድ ትልቅና አንድ ትንሽ አዳራሽ ለግልጋሎት ሲበቁ የ84 ሕንፃ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያንነት ውስጡ ከታደሰ በኋላ በየካቲት 15 ቀን 1989 ዓ.ም. (February 22, 1997) በአራት ሊቃነ ጳጳሳት እነዚህም ብፁዕ አቡነ ይሥሐቅ፣ በብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ በ ታቦተ ሕጉ ተባርኮ የመጀመሪያው ቅዳሴ ተደረገ።

አዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል

አዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል

የነበሩት ሕንፃዎች በቂ ባለመሆናቸውና የቤተክርስትያን ቅርፅ ያልነበረ ስለሆኑ ከሁለት ሺህ ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት የተከተለና ሰፋ ያለ ቦታ ያለው ቤተክርስትያን ለመሥራት የመጀመርያ ፕላን ቀርቦ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ የገንዘብ ስብሰባው ሥራ ጀመረ። በሁለት ሺህ ስድስት ዓ.ም. ኒኖ ሪኮ አርኪቴክት ድርጅት የሕንፃውን ፕላንና የማዘጋጃ ቤት ፈቃድ እንዲያገኝ ተመድቦ ሥራውን ጀምረ። ፈቃዱና የገንዘብ መሰባሰቡ ቀጥሎ  ኤፕሪል 18, 2010 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፡ ብፁዕ አቡነ መልከጼዲቅና በብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

ሥራውም በተቀላጠፈ ሁኔአታ ተጠናቆ በኅዳር ፰ ቀን ፪ሺህ፭ ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።