
ቀዳሚ ገጽ with image
እንኳን ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ድህረ ገፅ በሰላም መጡ።
ኢትዮጵያ የጁዲዮ የክርስትያን እምነትና ባሕል ያላት ጥንታዊት አገር ስትሆን የክርስትና እምነት ተከታዮች በብዛት የሚግኙባት ነች። አስገራሚ ታሪክ፣ ድንቅ ሥልጣኔዋ፣ባሕልና ሃይማኖታዊ የሆነው የሕዝቧችዋ አኗኗር ልዩ ያደርጋታል። በኦሪት ዘፍጥረት እንደተጻፈው “የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው፣እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።” (ዘፍ. 2፥13) በዳዊት መዝሙር ደግሞ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” (መዝ. 67(68)፥31)። ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ በብዙ የታሪክ መዛግብትና መጽሐፍት ላይ ስለ ኢትዮጵያ ተዘግቧል። በተጨማሪ ታሪካዊና አርኬኦሎጂካል ግኝቶች የሚያስገርሙ ሃቆችን ስለ ኢትዮጵያ እየገለጹ ነው። ኢትዮጵያ የራስዋ የሆነ ፊደል ከነአጻጻፉና ሥርዓቱ ጋር ያላት ብቸኛ አፍሪካዊት አገር ነች